ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ሚክያስ 1-7 ይሖዋ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? 6:6-8 ይሖዋ፣ አቅማችንን ያውቃል፤ መቼም ቢሆን ከአቅማችን በላይ የሆነ ነገር እንድናደርግ አይጠይቀንም። አምላክ፣ ከወንድሞቻችን ጋር ያለን ግንኙነት ለእሱ ከምናቀርበው አምልኮ ጋር ተያያዥነት እንዳለው እንድንገነዘብ ይፈልጋል። ይሖዋ መሥዋዕታችንን እንዲቀበለው ከፈለግን ለወንድሞቻችን ፍቅርና አክብሮት ሊኖረን ይገባል።