ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ማርቆስ 13-14
ሰውን መፍራት ወጥመድ እንዳይሆንባችሁ ተጠንቀቁ
ሐዋርያቱ በደረሰባቸው ጫና የተሸነፉት ለምንድን ነው?
በራሳቸው ከልክ በላይ ተማምነው ነበር። ሌላው ቀርቶ ጴጥሮስ ከሌሎቹ ሐዋርያት የበለጠ ለኢየሱስ ታማኝ እንደሆነ ተሰምቶት ነበር
ነቅተው መጠበቅና መጸለይ ተስኗቸው ነበር
ከስህተታቸው ትምህርት ያገኙት የኢየሱስ ሐዋርያት ጌታቸው ከሞት ከተነሳ በኋላ ሰውን መፍራት ወጥመድ እንዳይሆንባቸውና ተቃውሞ ቢኖርም በድፍረት መስበክ እንዲችሉ የረዳቸው ምንድን ነው?
የኢየሱስን ማስጠንቀቂያ በቁም ነገር ተመልክተውታል፤ በመሆኑም በደረሰባቸው ተቃውሞና ስደት አልተሸነፉም
በይሖዋ ታምነዋል እንዲሁም ጸልየዋል።—ሥራ 4:24, 29
ደፋር መሆናችንን ማሳየት የሚጠይቁ ምን ሁኔታዎች ያጋጥሙናል?