ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ሉቃስ 10-11
የደጉ ሳምራዊ ምሳሌ
ኢየሱስ ይህን ምሳሌ የተናገረው “ለመሆኑ ባልንጀራዬ ማን ነው?” በማለት ለቀረበለት ጥያቄ መልስ ለመስጠት ነው። (ሉቃስ 10:25-29) የክርስቲያን ጉባኤ ሳምራውያንንና አሕዛብን ጨምሮ “ሁሉንም ዓይነት ሰዎች” ያካተተ እንደሚሆን ያውቅ ነበር። (ዮሐ 12:32) ኢየሱስ በዚህ ምሳሌ አማካኝነት ተከታዮቹ ለሁሉም ሰዎች ሌላው ቀርቶ ከእነሱ በጣም የተለዩ ለሆኑ ሰዎች እንኳ ፍቅር ለማሳየት ለየት ያለ ጥረት ሊያደርጉ እንደሚገባ አስተምሯል።
ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦
‘ከእኔ የተለየ ባሕል ላላቸው ወንድሞችና እህቶች ምን አመለካከት አለኝ?’
‘አብዛኛውን ጊዜዬን የማሳልፈው ከእኔ ጋር ተመሳሳይ ሁኔታ ካላቸው ሰዎች ጋር ነው?’
‘ከእኔ የተለየ አስተዳደግ ካላቸው ክርስቲያኖች ጋር ይበልጥ ለመቀራረብ ጥረት በማድረግ ልቤን ወለል አድርጌ መክፈት እችላለሁ?’ (2ቆሮ 6:13)
ማንን ልጋብዝ እችላለሁ?
አገልግሎት
ቤቴ
በቤተሰብ አምልኳችን ላይ