ክርስቲያናዊ ሕይወት
አባካኙ ልጅ ተመለሰ!
አባካኙ ልጅ ተመለሰ! (እንግሊዝኛ) የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ዴቪድ ከእውነት ጎዳና እየራቀ እንደነበር የሚጠቁመው ምንድን ነው? ቤተሰቡና ሽማግሌዎች ሊረዱት የሞከሩት እንዴት ነው?
ወንድም ባርከርና ባለቤቱ ጥሩ ምሳሌ የሚሆኑ ወላጆች ናቸው የምንለው ለምንድን ነው?
ስለሚከተሉት ነገሮች ከዚህ ቪዲዮ ምን እንማራለን?
ሰብዓዊ ሥራ በሕይወታችን ውስጥ ትልቅ ቦታ እንዲይዝ ማድረግ ስላለው አደጋ
ስለ መጥፎ ጓደኝነት
ምክርን ስለመቀበል
ንስሐ የገቡትን ይቅር ስለማለት