የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb18 ነሐሴ ገጽ 3
  • የሎጥን ሚስት አስታውሱ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሎጥን ሚስት አስታውሱ
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2018
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሎጥን ሚስት አስታውሱ
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • የሎጥ ሚስት ወደ ኋላ ተመለከተች
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ከድህነት ወደ ብልጽግና
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018
  • ‘በኋላችሁ ያሉትን ነገሮች’ አትመልከቱ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2018
mwb18 ነሐሴ ገጽ 3
የሎጥ ሚስት ሰዶምን ዞር ብላ ስትመለከት የጨው ዓምድ ሆነች

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የሎጥን ሚስት አስታውሱ

የሎጥ ሚስት ከሰዶም እየሸሸች ሳለ ወደ ኋላ የተመለከተችው ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ የሚናገረው ነገር የለም። (ዘፍ 19:17, 26) ኢየሱስ ከሰጠው ማስጠንቀቂያ አውድ መረዳት እንደሚቻለው ትታ በወጣችው ቁሳዊ ነገር ላይ መጨከን አቅቷት ሊሆን ይችላል። (ሉቃስ 17:31, 32) እኛም እንደ ሎጥ ሚስት የአምላክን ሞገስ እንዳናጣ ምን ሊረዳን ይችላል? ሕይወታችን ቁሳዊ ነገሮችን በማሳደድ ላይ ያተኮረ እንዲሆን መፍቀድ አይኖርብንም። (ማቴ 6:33) ኢየሱስ “ለአምላክም ለሀብትም በአንድነት መገዛት አትችሉም” በማለት አስተምሯል። (ማቴ 6:24) ይሁንና በሕይወታችን ውስጥ ለቁሳዊ ነገሮች የምንሰጠው ቦታ ለመንፈሳዊ ነገሮች የምንሰጠውን ቦታ እየተሻማብን እንደሆነ ካስተዋልን ምን ማድረግ ይኖርብናል? በየትኞቹ አቅጣጫዎች ማስተካከያ ማድረግ እንዳለብን እንድናስተውል እንዲሁም እነዚህን ማስተካከያዎች ለማድረግ ድፍረትና ጥንካሬ እንድናገኝ ወደ ይሖዋ መጸለይ እንችላለን።

የሎጥን ሚስት አስታውሱ በተባለው ባለ ሦስት ክፍል ቪዲዮ ላይ የተመሠረቱትን የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • አና ሥራ ቦታ ሆና፤ ግሎሪያ ከአጎቷ ጋር፤ ብራያንና ግሎሪያ አብረው ሲጸልዩ

    “የሎጥን ሚስት አስታውሱ” የሚለውን ማስጠንቀቂያ ልብ እንዳልኩ በድርጊቴ ማሳየት የምችለው እንዴት ነው?

    ግሎሪያ ተጨማሪ ገንዘብ ለማግኘት እንድትጣጣር የተደረገባት ጫና በአስተሳሰቧ፣ በአነጋገሯና በድርጊቷ ላይ ተጽዕኖ ያሳደረው እንዴት ነው?

  • የሎጥ ሚስት በዛሬው ጊዜ ለሚገኙ ክርስቲያኖች የማስጠንቀቂያ ምሳሌ የምትሆነው እንዴት ነው?

  • ጆ እና ቤተሰቡ የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች ተግባራዊ በማድረጋቸው የተጠቀሙት እንዴት ነው?

  • አና ከሥራ ባልደረቦቿ ጋር የነበራት ቅርርብ በመንፈሳዊነቷ ላይ ተጽዕኖ ያሳደረው እንዴት ነው?

  • በሕይወታችን ውስጥ ለገንዘብ ቅድሚያ እንድንሰጥ የሚደረግብንን ጫና ለመቋቋም ድፍረት የሚያስፈልገን ለምንድን ነው?

  • ብራያንና ግሎሪያ በድጋሚ ለመንፈሳዊ ነገሮች ቅድሚያ መስጠት የጀመሩት እንዴት ነው?

  • በዚህ ቪዲዮ ላይ የትኞቹን የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች አስተውላችኋል?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ