ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ሉቃስ 19-20
ከአሥሩ ምናን ምሳሌ ምን ትምህርት እናገኛለን?
በዚህ ምሳሌ ውስጥ የተጠቀሱት ነገሮች ምን ያመለክታሉ?
መስፍኑ ኢየሱስን ያመለክታል
ባሪያዎቹ የኢየሱስን ቅቡዓን ደቀ መዛሙርት ያመለክታሉ
መስፍኑ ለባሪያዎቹ ሰጥቷቸው የሄደው ገንዘብ ውድ የሆነውን ደቀ መዛሙርት የማድረግ መብት ያመለክታል
ይህ ምሳሌ የኢየሱስ ቅቡዓን ደቀ መዛሙርት እንደ ክፉው ባሪያ ከሆኑ ምን ውጤት እንደሚጠብቃቸው የሚገልጽ ማስጠንቀቂያ ይዟል። ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ያላቸውን ማንኛውንም ነገር ተጨማሪ ደቀ መዛሙርት ለማፍራት እንዲጠቀሙበት ይጠብቅባቸዋል።
ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራ ታማኝ ቅቡዓን ክርስቲያኖችን መምሰል የምችለው እንዴት ነው?