ክርስቲያናዊ ሕይወት
እንደ ክርስቶስ ትሑቶችና ልካችሁን የምታውቁ ሁኑ
ኢየሱስ በምድር ላይ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ሰው ቢሆንም ይሖዋ እንዲከበር በማድረግ ትሑት እንደሆነና ልኩን እንደሚያውቅ አሳይቷል። (ዮሐ 7:16-18) በሌላ በኩል ግን ሰይጣን፣ “ስም አጥፊ” ማለትም ዲያብሎስ ሆኗል። (ዮሐ 8:44) ኩሩ የነበሩት ፈሪሳውያንም በመሲሑ ላይ እምነት የሚያሳድሩ ሰዎችን በማጣጣል የሰይጣን ዓይነት ዝንባሌ እንዳላቸው አሳይተዋል። (ዮሐ 7:45-49) በጉባኤ ውስጥ አንዳንድ መብቶች ወይም ኃላፊነቶች ሲሰጡን ኢየሱስ የተወውን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት ነው?
“እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ”—ቅናትና ጉራን አስወግዱ፣ ክፍል 1 የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተለውን ጥያቄ ለመመለስ ሞክር፦
አሌክስ ኩሩ እንደሆነ የሚያሳይ ምን ነገር አድርጓል?
“እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ”—ቅናትና ጉራን አስወግዱ፣ ክፍል 2 የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
አሌክስ ትሑት እንደሆነ ያሳየው እንዴት ነው?
አሌክስ፣ ቢልን እና ካርልን ያበረታታቸው እንዴት ነው?
“እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ”—ከትዕቢትና ጨዋነት ከጎደለው ምግባር ራቁ፣ ክፍል 1 የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተለውን ጥያቄ ለመመለስ ሞክር፦
ወንድም ሃሪስ ልኩን ማወቅ እንደተሳነው የሚያሳይ ምን ነገር አድርጓል?
“እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ”—ከትዕቢትና ጨዋነት ከጎደለው ምግባር ራቁ፣ ክፍል 2 የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ወንድም ሃሪስ ልኩን እንደሚያውቅ ያሳየው እንዴት ነው?
ወንድም ሃሪስ ከተወው ምሳሌ ፌይ ምን ትምህርት አግኝታለች?