ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | የሐዋርያት ሥራ 1-3
በክርስቲያን ጉባኤ ላይ መንፈስ ቅዱስ ፈሰሰ
በ33 ዓ.ም. በተከበረው የጴንጤቆስጤ በዓል ላይ የተገኙ በርካታ አይሁዳውያን ከሌሎች አገራት የመጡ ነበሩ። (ሥራ 2:9-11) እነዚህ አይሁዳውያን የሙሴን ሕግ ቢጠብቁም ሕይወታቸውን ሙሉ የኖሩት በባዕድ አገር ሊሆን ይችላል። (ኤር 44:1) በመሆኑም የአንዳንዶቹ አለባበስም ሆነ አነጋገር የመጡበትን አገር ሰዎች እንጂ የአይሁዳውያንን አይመስል ይሆናል። ከእነዚህ ሰዎች መካከል 3,000 የሚያህሉት በአንድ ጀምበር ሲጠመቁ፣ የክርስቲያን ጉባኤ የተለያየ ባሕልና አስተዳደግ ያላቸው ሰዎችን ያቀፈ ሆነ። የጉባኤው አባላት የተለያየ አስተዳደግና ባሕል ቢኖራቸውም ሁሉም “በአንድ ልብ ሆነው በቤተ መቅደሱ አዘውትረው ይገኙ ነበር።”—ሥራ 2:46
አንተስ ልባዊ አሳቢነት ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?
በክልልህ ውስጥ ለሚገኙ ከሌላ አገር የመጡ ሰዎች
በጉባኤህ ለሚገኙ ከሌላ አገር የመጡ ወንድሞችና እህቶች