ክርስቲያናዊ ሕይወት
“ለይሖዋ የሚሰጥ ስጦታ”
‘ዛሬ ለይሖዋ የሚሰጥ ስጦታ በእጃችን ይዘን መቅረብ’ የምንችለው እንዴት ነው? (1ዜና 29:5, 9, 14) የይሖዋ ምሥክሮች በአካባቢያችንም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያከናውኑትን ሥራ ለመደገፍ በፈቃደኝነት መዋጮ ማድረግ የምንችልባቸው የተለያዩ መንገዶች ከዚህ በታች ቀርበዋል።
በኢንተርኔት አማካኝነት የምንሰጠውም ሆነ በመዋጮ ሣጥኖች ውስጥ የምናስገባው ገንዘብ ጥቅም ላይ የሚውልባቸው መንገዶች፦
ለዓለም አቀፉ ሥራ
ቅርንጫፍ ቢሮዎችንና የርቀት የትርጉም ቢሮዎችን ለመገንባት ብሎም በዚያ የሚከናወነውን ሥራ ለማስኬድ
ለቲኦክራሲያዊ ትምህርት ቤቶች
ለልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች
በአደጋ የተጎዱትን ለመርዳት
ለሕትመት፣ ለቪዲዮዎችና በኤሌክትሮኒክ ፎርማት ለሚዘጋጁ ነገሮች
ለጉባኤ ወጪዎች
ለስብሰባ አዳራሹ በየጊዜው የሚወጡ ወጪዎችን ለመሸፈንና ለአዳራሹ ጥገና
ጉባኤው ለቅርንጫፍ ቢሮው እንዲላክ ድምፀ ውሳኔ ላደረገባቸው ለሚከተሉት ነገሮች፦
በዓለም ዙሪያ ለሚከናወን የጉባኤና የትላልቅ ስብሰባ አዳራሽ ግንባታ
ለዓለም አቀፍ የእገዛ ዝግጅት
ለሌሎች ዓለም አቀፋዊ እንቅስቃሴዎች
ትላልቅ ስብሰባዎች
በክልል ስብሰባችሁ ላይ የሚደረጉ መዋጮዎች ለዓለም አቀፉ ሥራ ይላካሉ። ከክልል፣ ከልዩና ከብሔራት አቀፍ ስብሰባዎች ጋር በተያያዘ የሚወጡ ወጪዎች የሚሸፈኑት ለዓለም አቀፉ ሥራ ከሚላከው ገንዘብ ነው።
ለወረዳዎች የሚደረጉ መዋጮዎች የስብሰባ ቦታ ለመከራየት፣ አዳራሹ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ለማሟላት እንዲሁም ከወረዳው ጋር የተያያዙ ሌሎች ወጪዎችን ለመሸፈን ይውላሉ። ወረዳዎች ወጪዎቻቸውን ከሸፈኑ በኋላ የሚተርፋቸውን ገንዘብ ዓለም አቀፉን የይሖዋ ምሥክሮች ሥራ ለመደገፍ ሊልኩ ይችላሉ።