የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb19 የካቲት ገጽ 3
  • የአምላክን የማይታዩ ባሕርያት ታስተውላለህ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአምላክን የማይታዩ ባሕርያት ታስተውላለህ?
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2019
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አስደናቂ የፍጥረት ሥራዎች የአምላክን ክብር ይገልጣሉ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
  • ፍጥረትን በማየት ስለ ይሖዋ ይበልጥ ተማሩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
  • ፍጥረትን በመጠቀም ልጆቻችሁን ስለ ይሖዋ አስተምሩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
  • ፍጥረት የይሖዋን ፍቅር የሚያሳየው እንዴት ነው?
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2019
mwb19 የካቲት ገጽ 3

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የአምላክን የማይታዩ ባሕርያት ታስተውላለህ?

በቀለማት ያሸበረቁ አበቦችን፣ በከዋክብት የተሞላውን ሰማይ ወይም እየተንዶለዶለ የሚወርድ ፏፏቴ ስትመለከት የፈጣሪን ሥራ ታደንቃለህ? የይሖዋን የማይታዩ ባሕርያት በዙሪያችን ካሉት ፍጥረታት በግልጽ መመልከት እንችላለን። (ሮም 1:20) በምናያቸው ነገሮች ላይ ቆም ብለን የምናሰላስል ከሆነ የአምላክን ኃይል፣ ፍቅር፣ ጥበብና ፍትሕ አልፎ ተርፎም ልግስናውን ማስተዋል እንችላለን።—መዝ 104:24

ከይሖዋ የፍጥረት ሥራዎች መካከል በየዕለቱ የትኞቹን የመመልከት አጋጣሚ አለህ? የምትኖረው ከተማ ውስጥ ቢሆንም እንኳ ወፎችን ወይም ዛፎችን ማየትህ አይቀርም። የይሖዋን የፍጥረት ሥራዎች በትኩረት መመልከታችን፣ ከልክ በላይ እንዳንጨነቅና ይበልጥ አስፈላጊ በሆኑት ነገሮች ላይ እንድናተኩር ይረዳናል፤ በተጨማሪም ይሖዋ እኛን ለዘላለም መንከባከብ እንደሚችል ያለንን እምነት ያጠናክረዋል። (ማቴ 6:25-32) ልጆች ካሏችሁ፣ ወደር የሌላቸውን የይሖዋ ባሕርያት እንዲያስተውሉ እርዷቸው። ለአምላክ የፍጥረት ሥራዎች ያለን አድናቆት እየጨመረ መሄዱ ወደ ፈጣሪያችን ይበልጥ እንድንቀርብ ያደርገናል።—መዝ 8:3, 4

አስደናቂ የፍጥረት ሥራዎች የአምላክን ክብር ይገልጣሉ—ብርሃን እና ቀለም የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ቀለማትን ለማየት የሚያስችለን ምንድን ነው?

  • ኢሬደሰንስ ምንድን ነው?

  • በሰማይ ላይ የተለያዩ ቀለማት የምናየው ለምንድን ነው?

  • በምትኖርበት አካባቢ በሚገኙ የፍጥረት ሥራዎች ላይ የትኞቹን አስደናቂ ቀለማት ተመልክተሃል?

  • የፍጥረት ሥራዎችን ጊዜ ወስደን መመልከታችን ምን ጥቅም አለው?

ሮዝ ጽጌረዳ፣ ሰማያዊ ቢራቢሮ፣ የተለያዩ ቀለማት ያላቸው ፍራፍሬዎች እንዲሁም ፀሐይ ስትጠልቅ፣ ሮዝ ጽጌረዳ

ብርሃንና ቀለም ስለ ይሖዋ ባሕርያት ምን ያስተምሩናል?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ