ክርስቲያናዊ ሕይወት
የእርዳታ አገልግሎታችን በካሪቢያን ደሴቶች ያሉ ክርስቲያኖችን የጠቀማቸው እንዴት ነው?
በመጀመሪያው መቶ ዘመን እንደነበረው ሁሉ በዛሬው ጊዜም አደጋ ለደረሰባቸው የእምነት ባልንጀሮቻችን ፍቅራችንን ማሳየት እንችላለን። (ዮሐ 13:34, 35) ክርስቲያኖች በካሪቢያን ደሴቶች ለሚገኙ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው እርዳታ ያደረጉት እንዴት እንደሆነ የሚያሳየውን ፍቅር በተግባር ሲደገፍ—በደሴቶች ላይ የተከናወነ የእርዳታ ሥራ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
በካሪቢያን የሚገኙት ወንድሞቻችን ኧርማ እና መሪያ በተባሉት ዝናብ የቀላቀሉ ኃይለኛ አውሎ ነፋሶች ምን ያህል ተጎድተዋል?
ይሖዋ በካሪቢያን ደሴቶች የሚገኙ ወንድሞቻችንን በእምነት ባልንጀሮቻቸው ተጠቅሞ የረዳቸው እንዴት ነው?
በአደጋው የተጎዱት ወንድሞች የእምነት ባልንጀሮቻቸው ያሳዩዋቸውን ፍቅርና ልግስና ሲመለከቱ ምን ተሰማቸው?
በካሪቢያን ደሴቶች አደጋ የደረሰባቸውን በመርዳቱ ሥራ ላይ ምን ያህል ወንድሞችና እህቶች ተካፍለዋል?
ሁላችንም በእርዳታ ሥራ መካፈል የምንችለው እንዴት ነው?
ይህን ቪዲዮ ስትመለከት አፍቃሪ በሆነው በዚህ ድርጅት ውስጥ በመታቀፍህ ምን ተሰማህ?