ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | 2 ተሰሎንቄ 1-3
የዓመፀኛው መገለጥ
ጳውሎስ በዚህ ጥቅስ ላይ የተናገረው ሐሳብ ምን ትርጉም አለው?
“የሚያግደው ነገር” (ቁ. 6)—ሐዋርያት ሳይሆኑ አይቀሩም
‘መገለጥ’ (ቁ. 6)—ሐዋርያት ከሞቱ በኋላ፣ ከሃዲ የሆኑ ክርስቲያኖች የሐሰት ትምህርቶችን በይፋ ማስተማር ጀመሩ፤ ግብዝነታቸውም በገሃድ ይታይ ጀመር
“ሚስጥራዊ የሆነው ይህ ዓመፅ” (ቁ. 7)—በጳውሎስ ዘመን “ዓመፀኛው” ማን እንደሆነ በግልጽ አይታወቅም ነበር
‘ዓመፀኛው’ (ቁ. 8)—በዛሬው ጊዜ፣ የሕዝበ ክርስትናን ቀሳውስት በቡድን ደረጃ ያመለክታል
‘ጌታ ኢየሱስ የእሱ መገኘት ይፋ በሚሆንበት ጊዜ ዓመፀኛውን እንዳልነበረ ያደርገዋል’ (ቁ. 8)—ኢየሱስ በሰይጣን ሥርዓት ላይ ይሖዋ የበየነውን ፍርድ በማስፈጸም፣ በሰማይ ንጉሥ ሆኖ መገኘቱን ይፋ ያደርጋል፤ የሚወስደው የፍርድ እርምጃ ‘ዓመፀኛውን’ ማጥፋትንም ይጨምራል
ይህ ጥቅስ በቅንዓትና በጥድፊያ ስሜት ለመስበክ የሚያነሳሳህ እንዴት ነው?