ክርስቲያናዊ ሕይወት
እነዚህን ነገሮች “ማሰባችሁን አታቋርጡ”
የትኞቹን ነገሮች? ፊልጵስዩስ 4:8 እውነት የሆነውን፣ ቁም ነገር ያለበትን፣ ጽድቅ የሆነውን፣ ንጹሕ የሆነውን፣ ተወዳጅ የሆነውን፣ በመልካም የሚነሳውን፣ በጎ የሆነውንና ምስጋና የሚገባውን ነገር እንድናስብ ያበረታታናል። እርግጥ ነው፣ ክርስቲያኖች ሁልጊዜ ስለ መንፈሳዊ ነገሮች ብቻ እንዲያስቡ አይገደዱም። ያም ቢሆን በልባችን የምናሰላስለው ነገር ይሖዋን ሊያስደስተው ይገባል። አስተሳሰባችን ለአምላክ ታማኝ ለመሆን ያደረግነውን ቁርጥ ውሳኔ ሊያዳክምብን አይገባም።—መዝ 19:14
ከመጥፎ ሐሳቦች መራቅ ቀላል አይደለም። ምክንያቱም ፍጹም ካልሆነው ሥጋችን ጋር ብቻ ሳይሆን “የዚህ ሥርዓት አምላክ” ከሆነው ከሰይጣን ጋርም መታገል ይጠበቅብናል። (2ቆሮ 4:4) በዓለማችን ውስጥ ያለውን መገናኛ ብዙኃን የሚቆጣጠረው ሰይጣን ስለሆነ በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮ፣ በኢንተርኔትና በጽሑፎች የሚገኘው አብዛኛው ነገር ወራዳ ነው። ወደ አእምሯችን በምናስገባቸው ነገሮች ረገድ ጠንቃቆች ካልሆንን አስተሳሰባችን ይበከላል፤ ውሎ አድሮ ደግሞ መጥፎ ድርጊት ልንፈጽም እንችላለን።—ያዕ 1:14, 15
ታማኝነትን የሚሸረሽሩ ነገሮችን አስወግዱ—ተገቢ ያልሆነ መዝናኛ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ወንድም በስልኩ ላይ የሚያየው ምን ነበር? ምን ተጽዕኖስ አሳድሮበታል?
በገላትያ 6:7, 8 እና በመዝሙር 119:37 ላይ ያለው ሐሳብ ወንድምን የረዳው እንዴት ነው?