ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | 1 ጴጥሮስ 3-5
“የሁሉም ነገር መጨረሻ ቀርቧል”
እስካሁን ድረስ በምድር ላይ ታይቶ የማያውቅ ታላቅ መከራ ከፊታችን ይጠብቀናል። ታዲያ አሁንም ሆነ ወደፊት በመንፈሳዊ ጠንካራ ሆነን መቀጠል የምንችለው እንዴት ነው?
ሳናሰልስ ሁሉንም የጸሎት ዓይነቶች በማቅረብ
ለወንድሞቻችንና ለእህቶቻችን የጠለቀ ፍቅር በማዳበርና ከምንጊዜውም ይበልጥ ከእነሱ ጋር በመቀራረብ
ሞቅ ያለ የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ በማሳየት
ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦ ‘በአካባቢዬም ሆነ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ወንድሞችና እህቶች ጥልቅ ፍቅርና ሞቅ ያለ የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ ማሳየት የምችልባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?’