ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፍጥረት 9-11
“ምድር ሁሉ አንድ ቋንቋ . . . ትጠቀም ነበር”
ይሖዋ በባቤል የነበሩትን ዓመፀኛ ሰዎች ቋንቋ በማዘበራረቅ ሰዎቹ ወደተለያየ ቦታ እንዲበታተኑ አድርጓል። በዛሬው ጊዜ ደግሞ ከሁሉም ብሔራትና ቋንቋዎች የተውጣጣን እጅግ ብዙ ሕዝብ አንድ ላይ በመሰብሰብና “ንጹሕ ቋንቋ” በመስጠት “የይሖዋን ስም እንዲጠሩና እጅ ለእጅ ተያይዘው እንዲያገለግሉት” እያደረገ ነው። (ሶፎ 3:9፤ ራእይ 7:9) ይህ “ንጹሕ ቋንቋ” በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ የሚገኘው ስለ ይሖዋና ስለ ዓላማው የሚገልጸው እውነት ነው።
አዲስ ቋንቋ መማር አዳዲስ ቃላትን ከማጥናት ያለፈ ነገርን ይጠይቃል። ከቀድሞው በተለየና አዲስ በሆነ መንገድ ማሰብን ይጨምራል። በተመሳሳይም የእውነትን ንጹሕ ቋንቋ ስንማር አእምሯችን ይታደሳል። (ሮም 12:2) ይህ ቀጣይ የሆነ ሂደት በአምላክ ሕዝቦች መካከል አንድነት እንዲኖር ያደርጋል።—1ቆሮ 1:10