ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፍጥረት 12-14
ሁላችንንም የሚመለከት ቃል ኪዳን
ይሖዋ ከአብርሃም ጋር ቃል ኪዳን የገባ ሲሆን ይህ ቃል ኪዳን በሰማይ ለተቋቋመው መንግሥት ሕጋዊ መሠረት ጥሏል
ከሁኔታዎች መረዳት እንደሚቻለው፣ ቃል ኪዳኑ ሥራ ላይ መዋል የጀመረው በ1943 ዓ.ዓ. አብርሃም ወደ ከነአን ሲጓዝ የኤፍራጥስን ወንዝ በተሻገረበት ጊዜ ነው
ቃል ኪዳኑ ሥራ ላይ መዋሉን የሚቀጥለው መሲሐዊው መንግሥት የአምላክን ጠላቶች አጥፍቶ ለምድር ሕዝቦች ሁሉ በረከት እስኪያመጣ ድረስ ነው
አብርሃም ጠንካራ እምነት እንዳለው በማሳየቱ ይሖዋ ባርኮታል። እኛስ ይሖዋ ቃል በገባቸው ነገሮች ላይ እምነት እንዳለን ካሳየን በአብርሃም ቃል ኪዳን አማካኝነት የትኞቹን በረከቶች እናገኛለን?