ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፍጥረት 25-26
ኤሳው የብኩርና መብቱን ሸጠ
ኤሳው ‘ለቅዱስ ነገሮች አድናቆት’ አልነበረውም። (ዕብ 12:16) በዚህም ምክንያት የብኩርና መብቱን ሸጧል። በተጨማሪም ይሖዋን የማያመልኩ ሁለት ሴቶችን አግብቷል።—ዘፍ 26:34, 35
ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ከታች ለተጠቀሱት ቅዱስ ነገሮች ከፍተኛ አድናቆት እንዳለኝ ማሳየት የምችለው እንዴት ነው?’
ከይሖዋ ጋር ለመሠረትኩት ዝምድና
ለመንፈስ ቅዱስ
የይሖዋን ቅዱስ ስም የመሸከም መብት
ለመስክ አገልግሎት
ለክርስቲያናዊ ስብሰባዎች
ለትዳር