ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፍጥረት 44–45
ዮሴፍ ወንድሞቹን ይቅር አላቸው
ሌሎችን ይቅር ማለት ከባድ ሊሆን ይችላል፤ በተለይ ግለሰቡ የጎዳን ሆን ብሎ ከሆነ ይቅር ማለት ይበልጥ ሊከብደን ይችላል። ዮሴፍ ወንድሞቹ ከባድ በደል ቢያደርሱበትም ይቅር እንዲላቸው የረዳው ምንድን ነው?
ዮሴፍ ወንድሞቹን ከመበቀል ይልቅ ይቅር ለማለት የሚያስችል ምክንያት ፈልጓል።—መዝ 86:5፤ ሉቃስ 17:3, 4
ቂም አልያዘም፤ ከዚህ ይልቅ ይቅርታው ብዙ የሆነውን ይሖዋን መስሏል።—ሚክ 7:18, 19
ይቅር ባይ በመሆን ረገድ ይሖዋን መምሰል የምችለው እንዴት ነው?