ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፀአት 10–11
ሙሴና አሮን ታላቅ ድፍረት አሳይተዋል
ሙሴና አሮን በዘመኑ ከነበሩት ሰዎች ሁሉ እጅግ ኃያል የሆነውን ፈርዖንን ሲያነጋግሩ ታላቅ ድፍረት አሳይተዋል። ይህን ማድረግ የቻሉት እንዴት ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሙሴ ሲናገር “በእምነት ግብፅን ለቆ ወጣ፤ ሆኖም ይህን ያደረገው የንጉሡን ቁጣ ፈርቶ አይደለም፤ የማይታየውን አምላክ እንደሚያየው አድርጎ በጽናት ቀጥሏልና” ይላል። (ዕብ 11:27) ሙሴና አሮን በይሖዋ ላይ ጠንካራ እምነት ነበራቸው፤ እንዲሁም በእሱ ይተማመኑ ነበር።
ሥልጣን ላለው ሰው እምነትህን በድፍረት መናገር የሚጠይቁ ሁኔታዎች የትኞቹ ናቸው?