ክርስቲያናዊ ሕይወት
ፍጥረት ስለ ድፍረት ምን ያስተምረናል?
ይሖዋ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጠቀሱ ወንዶችና ሴቶች አማካኝነት ክርስቲያናዊ ባሕርያትን እንድናዳብር ያስተምረናል። ይህ ብቻ ሳይሆን ከፍጥረት ሥራዎቹም ብዙ ትምህርት እናገኛለን። (ኢዮብ 12:7, 8) ከአንበሳ፣ ከፈረስ፣ ከሞንጉስ፣ ከሃሚንግበርድና ከዝሆን ስለ ድፍረት ምን እንማራለን?
ከፍጥረት ድፍረትን ተማሩ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
እንስት አንበሶች ደቦሎቻቸውን ከጥቃት ለመጠበቅ ድፍረት የሚያሳዩት እንዴት ነው?
ፈረሶች በውጊያ ወቅት ድፍረት እንዲያሳዩ የሚሠለጥኑት እንዴት ነው?
ሞንጉስ መርዘኛ እባቦችን የማይፈራው ለምንድን ነው?
በጣም ትናንሽ የሆኑት ሃሚንግበርዶች ድፍረት የሚያሳዩት እንዴት ነው?
ዝሆኖች የመንጋቸውን አባላት በድፍረት ከጥቃት የሚከላከሉት እንዴት ነው?
ድፍረትን በተመለከተ ከእነዚህ እንስሳት ምን ትምህርት አግኝተሃል?