ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፀአት 13–14
‘ጸንታችሁ ቁሙ፤ ይሖዋ የሚፈጽመውን ማዳን እዩ’
ይሖዋ ሕዝቦቹን የሚያድነው አሳቢነት በሚንጸባረቅበት መንገድ ነው። እስራኤላውያን ከግብፅ ሲወጡ በግለሰብ ደረጃ አሳቢነት ያሳያቸው በምን መንገድ ነው?
አደራጅቷቸዋል።—ዘፀ 13:18
አመራር ሰጥቷቸዋል፤ ጥበቃም አድርጎላቸዋል።—ዘፀ 14:19, 20
ልጆችንና አረጋውያንን ጨምሮ ሕዝቦቹን በሙሉ አድኗቸዋል።—ዘፀ 14:29, 30
ታላቁ መከራ እየቀረበ ሲመጣ ስለ ምን ነገር እርግጠኛ መሆን ትችላለህ?—ኢሳ 30:15