የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb20 ጥቅምት ገጽ 3
  • ከይሖዋ ጋር ያላችሁን ዝምድና ከፍ አድርጋችሁ ተመልከቱ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከይሖዋ ጋር ያላችሁን ዝምድና ከፍ አድርጋችሁ ተመልከቱ
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2020
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከጣዖት አምልኮ መጠበቅ የሚገባን ለምንድን ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ራሳችሁን ከማንኛውም ዓይነት የጣዖት አምልኮ ጠብቁ
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ከይሖዋ ጋር ያለህ ወዳጅነት ምን ያህል ጠንካራ ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ሌሎች ሰዎች ይሖዋን እንዲወዱ አስተምሯቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2020
mwb20 ጥቅምት ገጽ 3
ሥዕሎች፦ አንድ ሰው ከይሖዋ ጋር ያለውን ዝምድና ሲያጠናክር። 1. ሲጸልይ። ወደ ላይ የሚያመለክት ቀስት። 2. መጽሐፍ ቅዱስ ሲያነብ። ወደ ታች የሚያመለክት ቀስት።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ከይሖዋ ጋር ያላችሁን ዝምድና ከፍ አድርጋችሁ ተመልከቱ

የይሖዋ ምሥክር መሆን ልዩ መብት ያስገኛል። ራሳችንን ወስነን የተጠመቅን ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን ከሉዓላዊው ጌታ ከይሖዋ ጋር በግለሰብ ደረጃ የቅርብ ዝምድና መመሥረት ችለናል። ይሖዋ በልጁ አማካኝነት ወደ ራሱ ስቦናል። (ዮሐ 6:44) ጸሎታችንንም ይሰማል።—መዝ 34:15

ከይሖዋ ጋር ያለን ውድ ዝምድና እንዳይበላሽ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? እንደ እስራኤላውያን የኃጢአት ጎዳና እንዳንከተል መጠንቀቅ ይኖርብናል። እስራኤላውያን ከይሖዋ ጋር ቃል ኪዳን ከገቡ ብዙም ሳይቆይ የወርቅ ጥጃ በመሥራት ጣዖት አምልከዋል። (ዘፀ 32:7, 8፤ 1ቆሮ 10:7, 11, 14) ራሳችንን እንደሚከተለው እያልን መጠየቅ እንችላለን፦ ‘መጥፎ ነገር ለማድረግ ስፈተን ምን ምላሽ እሰጣለሁ? ድርጊቴ ከይሖዋ ጋር ያለኝን ዝምድና ከፍ አድርጌ እንደምመለከተው ያሳያል?’ ለሰማዩ አባታችን ያለን ጥልቅ ፍቅር እሱ ከሚጠላቸው ነገሮች እንድንሸሽ ያነሳሳናል።—መዝ 97:10

ከይሖዋ ጋር ያላችሁ ዝምድና እንዳይበላሽ ተጠንቀቁ (ቆላ 3:5) የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ስግብግብነት ምንድን ነው?

  • ከስግብግብነትና ከጣዖት አምልኮ መራቅ ያለብን ለምንድን ነው?

  • በምንዝርና በጣዖት አምልኮ መካከል ያለው ተመሳሳይነት ምንድን ነው?

  • በተለይ ቲኦክራሲያዊ ኃላፊነት ያላቸው ሰዎች ለትዳር ጓደኛቸው ፍላጎት ትኩረት መስጠት ያለባቸው ለምንድን ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ