ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘሌዋውያን 1–3
መባዎች የሚቀርቡበት ዓላማ
በሕጉ ቃል ኪዳን ሥር ይቀርቡ የነበሩት መባዎች ወይም መሥዋዕቶች ይሖዋን ያስደስቱ የነበረ ከመሆኑም ሌላ ኢየሱስ ላቀረበው ቤዛዊ መሥዋዕት ወይም ይህ መሥዋዕት ለሚያስገኘው ጥቅም ምሳሌ ሆነው አገልግለዋል።—ዕብ 8:3-5፤ 9:9፤ 10:5-10
መሥዋዕት ሆነው የሚቀርቡት እንስሳት በሙሉ ጤናማና እንከን የለሽ መሆን እንደነበረባቸው ሁሉ ኢየሱስም ያቀረበው ፍጹምና እንከን የለሽ የሆነውን አካሉን ነው።—1ጴጥ 1:18, 19
የሚቃጠሉ መባዎች ሙሉ በሙሉ ለአምላክ ይቀርቡ እንደነበረ ሁሉ ኢየሱስም ራሱን ሙሉ በሙሉ ለይሖዋ ሰጥቷል
ተቀባይነት ያለው የኅብረት መሥዋዕት የሚያቀርቡ ሰዎች ከአምላክ ጋር ሰላማዊ ግንኙነት እንደነበራቸው ሁሉ በጌታ ራት የሚካፈሉት ቅቡዓንም ከአምላክ ጋር ሰላማዊ ግንኙነት አላቸው