የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb20 ታኅሣሥ ገጽ 3
  • ይሖዋ ተግሣጽ የሚሰጥበትን መንገድ በመደገፍ ፍቅር እናሳያለን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይሖዋ ተግሣጽ የሚሰጥበትን መንገድ በመደገፍ ፍቅር እናሳያለን
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2020
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ተግሣጽ የይሖዋ የፍቅር መግለጫ ነው
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • ውገዳ ፍቅራዊ ዝግጅት ነው ሊባል የሚችለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • የቤተሰባችሁ አባል ይሖዋን ሲተው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2021
  • ታማኝነት የሚያስከትለውን ፈተና መቋቋም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2020
mwb20 ታኅሣሥ ገጽ 3

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ይሖዋ ተግሣጽ የሚሰጥበትን መንገድ በመደገፍ ፍቅር እናሳያለን

ውገዳ ለጉባኤው ጥበቃ ይሆናል፤ ንስሐ ለመግባት ፈቃደኛ ያልሆነው ሰውም ተገቢውን ተግሣጽ እንዲያገኝ ያደርጋል። (1ቆሮ 5:6, 11) ይሖዋ ተግሣጽ የሚሰጥበትን ይህን ዝግጅት የምንደግፍ ከሆነ ፍቅር እናሳያለን። ውገዳ የቅርብ የቤተሰብ አባላትንና የፍርድ ኮሚቴውን አባላት ጨምሮ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ሰዎች ሁሉ ላይ ሐዘን ሊያስከትል ይችላል፤ በዚህ ጊዜም ዝግጅቱን መደገፋችን ፍቅራችንን የሚያሳየው እንዴት ነው?

ከሁሉ በላይ፣ ለይሖዋ ስምና ለቅድስና መሥፈርቱ ፍቅር እንዳለን ያሳያል። (1ጴጥ 1:14-16) ለተወገደው ሰው ያለንን ፍቅርም ያሳያል። ጠንከር ያለ ተግሣጽ ሐዘን የሚያስከትል ቢሆንም ግለሰቡ “የጽድቅን ሰላማዊ ፍሬ” እንዲያፈራ ሊያደርገው ይችላል። (ዕብ 12:5, 6, 11) ከተወገደ ወይም ራሱን ካገለለ ሰው ጋር ያለንን ግንኙነት ከቀጠልን ይሖዋ ለሚሰጠው ተግሣጽ እንቅፋት እንሆናለን። ይሖዋ ሕዝቡን የሚገሥጸው “በተገቢው መጠን” እንደሆነ አስታውሱ። (ኤር 30:11) ግለሰቡ ወደ መሐሪው አባታችን እንደሚመለስ ተስፋ እናደርጋለን፤ እስከዚያው ግን ይሖዋ የሚሰጠውን ተግሣጽ እንደግፍ እንዲሁም መንፈሳዊ ልማዳችንን ይዘን እንቀጥል።—ኢሳ 1:16-18፤ 55:7

ባልተከፋፈለ ልብ ታማኝነትን ጠብቁ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ‘ባልተከፋፈለ ልብ ታማኝነትን ጠብቁ’ ከተባለው ቪዲዮ ላይ የተወሰደ ምስል። ገብሪዬላ እና ቤን ከቤት ዓምፆ የወጣው ልጃቸው የጻፈውን ደብዳቤ ካነበቡ በኋላ በሐዘን ተደቁሰው።

    ክርስቲያን ወላጆች፣ ልጃቸው ይሖዋን ሲተው ምን ይሰማቸዋል?

  • ‘ባልተከፋፈለ ልብ ታማኝነትን ጠብቁ’ ከተባለው ቪዲዮ ላይ የተወሰደ ምስል። ወንድሞችና እህቶች ከስብሰባ በኋላ ገብሪዬላን እና ቤንን አቅፈው ሲያጽናኗቸው።

    ጉባኤው፣ ታማኝ የሆኑትን የቤተሰብ አባላት መደገፍ የሚችለው እንዴት ነው?

  • ‘ባልተከፋፈለ ልብ ታማኝነትን ጠብቁ’ ከተባለው ቪዲዮ ላይ የተወሰደ ምስል። ገብሪዬላ ስለ ቆሬ ዓመፅ የሚናገረውን ታሪክ በዓይነ ሕሊናዋ ስትመለከት።

    ለይሖዋ ያለን ታማኝነት፣ ለቤተሰባችን ካለን ታማኝነት ሊበልጥ እንደሚገባ የሚያጎላው የትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ነው?

  • ‘ባልተከፋፈለ ልብ ታማኝነትን ጠብቁ’ ከተባለው ቪዲዮ ላይ የተወሰደ ምስል። ከስብሰባ በኋላ ገብሪዬላ ከልጃቸው ስለተላከላት የጽሑፍ መልእክት ለቤን ስትነግረው።

    ከቤተሰባችን ይልቅ ለይሖዋ ታማኝ እንደሆንን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ