ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘሌዋውያን 12–13
የሥጋ ደዌን በተመለከተ ከተሰጡት ሕጎች የምናገኘው ትምህርት
የሥጋ ደዌን በተመለከተ ከተሰጡት ሕጎች በስተጀርባ ያሉት መሠረታዊ ሥርዓቶች መንፈሳዊ ጤንነታችንን ስለ መጠበቅ ምን ያስተምሩናል?
ይሖዋ፣ የሥጋ ደዌው ሳይስፋፋ ቶሎ ማወቅ የሚችሉበትን መንገድ ለካህናቱ አስተምሯቸዋል። በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያን እረኞችም መንፈሳዊ እርዳታ የሚያስፈልገውን ሰው ወዲያውኑ ትኩረት ሰጥተው ይረዱታል።—ያዕ 5:14, 15
እስራኤላውያን የሥጋ ደዌ በሽታ እንዳይስፋፋ ለመከላከል ሲሉ በበሽታው የተበከለን ማንኛውም ዕቃ ያቃጥሉ ነበር። ክርስቲያኖችም ለእነሱ ምንም ያህል ውድ ቢሆን ወደ ኃጢአት ሊመራ የሚችልን ማንኛውም ነገር ማስወገድ ይኖርባቸዋል። (ማቴ 18:8, 9) ይህም ልማዶቻቸውን፣ ጓደኞቻቸውን ወይም የሚመርጡትን መዝናኛ ይጨምራል
አንድ ክርስቲያን የይሖዋን እርዳታ የመቀበል ልባዊ ፍላጎት እንዳለው ማሳየት የሚችለው እንዴት ነው?