ክርስቲያናዊ ሕይወት
በመንግሥቱ ወንጌላውያን ትምህርት ቤት መማር ትፈልጋለህ?
ከ23 እስከ 65 ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የምትገኝና በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ ያለህ ክርስቲያን ነህ? ጥሩ ጤንነት አለህ? ሰባኪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ወደ የትኛውም አካባቢ ተዛውረህ ለማገልገል ሁኔታህ ይፈቅድልሃል? ለእነዚህ ጥያቄዎች አዎ የሚል መልስ ከሰጠህ የመንግሥቱ ወንጌላውያን ትምህርት ቤት ገብተህ ለመማር አስበህ ታውቃለህ? ከመጀመሪያው ክፍል አንስቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ባለትዳሮች እንዲሁም ነጠላ ወንድሞችና እህቶች በትምህርት ቤቱ ለመማር አመልክተዋል። ይሁንና ተጨማሪ ነጠላ ወንድሞች ያስፈልጉናል። እንግዲያው ይሖዋን ለማስደሰትና ልጁን ለመምሰል ያለህ ፍላጎት ይበልጥ እንዲጨምር ጸልይ። (መዝ 40:8፤ ማቴ 20:28፤ ዕብ 10:7) ከዚያም ከሥራህ ወይም ከግል ሕይወትህ ጋር በተያያዘ ግዴታ ውስጥ ገብተህ ከሆነ ማስተካከያ ማድረግ የምትችልባቸውን መንገዶች ፈልግ።
ከዚህ ትምህርት ቤት የተመረቁ ክርስቲያኖች የትኞቹ የአገልግሎት አጋጣሚዎች ተከፍተውላቸዋል? አንዳንድ ተመራቂዎች ሌላ ቋንቋ በሚነገርበት ክልል እንዲያገለግሉ ወይም በልዩ የአደባባይ ምሥክርነት እንዲካፈሉ ተመድበዋል። ሌሎቹ ደግሞ ከጊዜ በኋላ ተተኪ የወረዳ የበላይ ተመልካች፣ የወረዳ የበላይ ተመልካች ወይም የመስክ ሚስዮናዊ ሆነው የማገልገል መብት አግኝተዋል። በይሖዋ አገልግሎት ልታከናውናቸው የምትችላቸውን ነገሮች ስታስብ እንደ ነቢዩ ኢሳይያስ “እነሆኝ! እኔን ላከኝ!” ለማለት ትገፋፋ ይሆናል።—ኢሳ 6:8
የመስክ ሚስዮናውያን—በመከሩ ሥራ የሚካፈሉ ሠራተኞች የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
የመስክ ሚስዮናውያን የሚመረጡት እንዴት ነው?
የመስክ ሚስዮናውያን የትኛውን መልካም ሥራ እያከናወኑ ነው?
የሚስዮናዊነት አገልግሎት የሚያስገኛቸው አንዳንድ በረከቶች የትኞቹ ናቸው?