ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
ሕጉ፣ ይሖዋ ለእንስሳት ያለውን አሳቢነት የሚያሳየው እንዴት ነው?
እርዳታ የሚያስፈልገውን እንስሳ ችላ ብሎ ማለፍ የተወገዘ ነበር (ዘዳ 22:4፤ it-1 375-376)
ጫጩቶች ወይም እንቁላሎች የታቀፈችን ወፍ መውሰድ የተወገዘ ነበር (ዘዳ 22:6, 7፤ it-1 621 አን. 1)
ሕጉ፣ የተለያዩ እንስሳትን አንድ ላይ መጥመድን ይከለክል ነበር (ዘዳ 22:10፤ w03 10/15 32 አን. 1-2)
እንስሳትን የምንይዝበት መንገድ ከይሖዋ ጋር ያለንን ግንኙነት ይነካዋል። በእንስሳት ላይ የጭካኔ ድርጊት መፈጸም ወይም ለመዝናኛ ስንል እንስሳትን መግደል አይኖርብንም።—ምሳሌ 12:10