በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር | በአገልግሎት የምታገኙትን ደስታ አሳድጉ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁ ራሳቸውን በመንፈሳዊ እንዲመግቡ እርዷቸው
ጥናቶቻችን መንፈሳዊ ፍላጎታቸውን እንዲያረኩና መንፈሳዊ ጉልምስና ላይ እንዲደርሱ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን ከእኛ ከመማር ያለፈ ነገር ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። (ማቴ 5:3፤ ዕብ 5:12–6:2) በመንፈሳዊ ራሳቸውን መመገብ የሚችሉበትን መንገድ መማር አለባቸው።
ገና ከመጀመሪያው አንስቶ ጥናቶቻችሁን ለጥናታቸው እንዴት እንደሚዘጋጁ አሳዩአቸው፤ እንዲሁም ተዘጋጅተው እንዲመጡ አበረታቷቸው። (mwb18.03 6) መጽሐፍ ቅዱስን በግላቸው በሚያጠኑበት ወቅት ሁልጊዜ በቅድሚያ እንዲጸልዩ አበረታቷቸው። በኤሌክትሮኒክ ፎርማት የተዘጋጁ ለጥናት የሚረዱ መሣሪያዎችን እንዴት እንደሚያገኙና እንደሚጠቀሙ አሳዩአቸው። jw.org እና JW ብሮድካስቲንግ ላይ የሚወጡ አዳዲስ ነገሮችን መከታተል የሚችሉት እንዴት እንደሆነ አስረዷቸው። በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያነቡ፣ ለጉባኤ ስብሰባዎች እንዲዘጋጁና ለጥያቄዎቻቸው መልስ ለማግኘት ምርምር እንዲያደርጉ ደረጃ በደረጃ አሠልጥኗቸው። በተማሩት ነገር ላይ እንዴት እንደሚያሰላስሉ አስተምሯቸው።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁን እርዷቸው—ራሳቸውን በመንፈሳዊ እንዲመግቡ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ኒታ፣ ጥናት ሲባል የጥያቄዎቹን መልስ ማግኘት ማለት ብቻ እንዳልሆነ እንድትገነዘብ ጄድን የረዳቻት እንዴት ነው?
ጄድ፣ ይሖዋ የፆታ ብልግናን መከልከሉ ተገቢ እንደሆነ እንድታምን የረዳት ምንድን ነው?
ጥናቶቻችሁ አእምሯቸውንና ልባቸውን መመገብ የሚችሉበትን መንገድ አስተምሯቸው
ጄድ ማሰላሰልን በተመለከተ ምን መገንዘብ ችላለች?