በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር | በአገልግሎት የምታገኙትን ደስታ አሳድጉ
ጥያቄዎችን ተጠቀሙ
“ደስተኛው አምላክ” ይሖዋ በአገልግሎታችን ደስታ እንድናገኝ ይፈልጋል። (1ጢሞ 1:11) ክህሎታችንን ለማሳደግ ጥረት ባደረግን መጠን ደስታችንም ይጨምራል። ጥያቄ መጠየቅ የሰዎችን የማወቅ ፍላጎት ለመቀስቀስ እንዲሁም በቀላሉ ውይይት ለመጀመር ያስችላል። ጥያቄዎች ሰዎች እንዲያስቡና እንዲያመዛዝኑ ለማድረግ ይረዳሉ። (ማቴ 22:41-45) ጥያቄ መጠየቃችንና ግለሰቡ መልስ ሲሰጥ ማዳመጣችን ለግለሰቡ ትልቅ ቦታ እንደምንሰጠው ያሳያል። (ያዕ 1:19) ግለሰቡ የሚሰጠው መልስ ውይይቱን እንዴት መቀጠል እንዳለብን ለመወሰን ሊረዳን ይችላል።
ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ የሚያስገኘውን ደስታ አጣጥሙ—ክህሎታችሁን አሻሽሉ—ጥያቄዎችን መጠቀም የሚለውን አጭር ድራማ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ጄድ የትኞቹን መልካም ባሕርያት አሳይታለች?
ኒታ ለጄድ ትኩረት እንደሰጠቻት ለማሳየት ጥያቄዎችን የተጠቀመችው እንዴት ነው?
ኒታ ጄድ ለምሥራቹ ፍላጎት እንዲኖራት ለመርዳት ጥያቄዎችን የተጠቀመችው እንዴት ነው?
ኒታ ጄድ እንድታስብና እንድታመዛዝን ለመርዳት ጥያቄዎችን የተጠቀመችው እንዴት ነው?