በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር | በአገልግሎት የምታገኙትን ደስታ አሳድጉ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁን በስብሰባዎች ላይ እንዲገኙ እርዷቸው
የጉባኤ ስብሰባዎች የንጹሑ አምልኮ ወሳኝ ገጽታ ናቸው። (መዝ 22:22) ይሖዋን ለማምለክ የሚሰበሰቡ ሁሉ ደስታና በረከት ያገኛሉ። (መዝ 65:4) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች በስብሰባዎች ላይ አዘውትረው የሚገኙ ከሆነ ብዙውን ጊዜ እድገታቸው ይፋጠናል።
ታዲያ ጥናቶቻችሁ በስብሰባ ላይ እንዲገኙ መርዳት የምትችሉት እንዴት ነው? በስብሰባ ላይ እንዲገኙ በተደጋጋሚ ግብዣ አቅርቡላቸው። በስብሰባ አዳራሻችን ውስጥ ምን ይከናወናል? የሚለውን ቪዲዮ አሳዩአቸው። የስብሰባዎችን ጥቅም አስረዷቸው። (lff ምዕራፍ 10) ባለፈው ስብሰባ ላይ ምን እንደተማራችሁ ወይም በቀጣዩ ስብሰባ ላይ ምን ትምህርት እንደሚቀርብ ንገሯቸው። በስብሰባ ላይ የሚጠናውን ጽሑፍ ለጥናቶቻችሁ ስጧቸው። በተጨማሪም ተግባራዊ እርዳታ አድርጉላቸው። ምናልባት ወደ ስብሰባ የሚወስዳቸው ሰው ያስፈልጋቸው ይሆናል። ጥናታችሁ ለመጀመሪያ ጊዜ ስብሰባ ላይ ሲገኝ በዚህ ረገድ ለከፈላችሁት መሥዋዕትነት ሁሉ ትካሳላችሁ።—1ቆሮ 14:24, 25
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁን በስብሰባዎች ላይ እንዲገኙ እርዷቸው የሚለውን አጭር ድራማ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ኒታ፣ ጄድን ወደ ስብሰባ ለመጋበዝ የትኛውን አጋጣሚ ተጠቅማለች?
ጥናታችን ስብሰባ ላይ ሲገኝ የምንደሰተው ለምንድን ነው?
“አምላክ በእርግጥ በመካከላችሁ ነው”
ጄድ ለመጀመሪያ ጊዜ ስብሰባ ላይ ስትገኝ ምን ተሰማት?