የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb23 ሐምሌ ገጽ 11
  • ለቤተሰባችሁ ደስታ አስተዋጽኦ ማበርከት ትችላላችሁ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለቤተሰባችሁ ደስታ አስተዋጽኦ ማበርከት ትችላላችሁ
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አንዲት እናት የሰጠችው ጥበብ ያዘለ ምክር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • ቤተሰብህ ደስተኛ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው?
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • ተግሣጽ የይሖዋ የፍቅር መግለጫ ነው
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች ተጠቅማችሁ ልጆቻችሁ እንዲሳካላቸው እርዷቸው
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
mwb23 ሐምሌ ገጽ 11
ምስሎች፦ “ቤተሰባችሁ ደስተኛ እንዲሆን አድርጉ” በሚለው ቪዲዮ ላይ የተመሠረቱ ሥዕሎች። 1. ወላጆች በደስታ ኬክ ሲበሉ ልጆቻቸው ሲያዩ። 2. ልጆቹ በቤተሰብ አምልኮ ወቅት ሲሳሳቁ። 3. እናትየዋ ታማ ሶፋ ላይ ተኝታ ሳለ አንደኛዋ ልጅ ስታስታምማት።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ለቤተሰባችሁ ደስታ አስተዋጽኦ ማበርከት ትችላላችሁ

ይሖዋ ቤተሰቦች ደስተኛ እንዲሆኑ ይፈልጋል። (መዝ 127:3-5፤ መክ 9:9፤ 11:9) ይሁንና በዚህ ዓለም ውስጥ ያለው ውጥረት እንዲሁም የቤተሰባችን አባላት የሚሠሩት ስህተት ደስታችንን ሊያደፈርሰው ይችላል። ታዲያ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ለቤተሰቡ ደስታ አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችለው እንዴት ነው?

ባል ሚስቱን ሊያከብራት ይገባል። (1ጴጥ 3:7) ከእሷ ጋር ጊዜ ያሳልፋል። ከእሷ በሚጠብቀው ነገር ረገድ ሚዛናዊ ነው፤ እንዲሁም ለእሱና ለቤተሰቡ ለምታደርገው ነገር ያደንቃታል። (ቆላ 3:15) ፍቅሩን ይገልጽላታል፤ እንዲሁም ያሞግሳታል።—ምሳሌ 31:28, 31

ሚስት ደግሞ ባሏን በተለያዩ መንገዶች ትደግፋለች። (ምሳሌ 31:12) ትገዛለታለች፤ እንዲሁም ትተባበረዋለች። (ቆላ 3:18) እሱን ስታነጋግርም ሆነ ስለ እሱ ስትናገር ደግነት ታሳያለች።—ምሳሌ 31:26

ወላጆች ለልጆቻቸው ጊዜያቸውን ይሰጣሉ። (ዘዳ 6:6, 7) እንደሚወዷቸው ይነግሯቸዋል። (ማቴ 3:17) ለልጆቻቸው ተግሣጽ የሚሰጡት በፍቅርና በማስተዋል ነው።—ኤፌ 6:4

ልጆች ወላጆቻቸውን ያከብራሉ፤ እንዲሁም ይታዘዙላቸዋል። (ምሳሌ 23:22) የሚያስቡትንና የሚሰማቸውን ለወላጆቻቸው ይናገራሉ። ወላጆቻቸው የሚሰጧቸውን ተግሣጽ ይቀበላሉ፤ እንዲሁም አክብሮት ያሳዩአቸዋል።—ምሳሌ 19:20

ቤተሰባችሁ ደስተኛ እንዲሆን አድርጉ የሚለውን አጭር ድራማ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተለውን ጥያቄ ለመመለስ ሞክር፦

እያንዳንዱ የቤተሰቡ አባል ለቤተሰቡ ደስታ አስተዋጽኦ ያበረከተው እንዴት ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ