የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb23 መስከረም ገጽ 13
  • ሃይማኖት የሌላቸው ሰዎች ፈጣሪያቸውን እንዲያውቁ እርዷቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሃይማኖት የሌላቸው ሰዎች ፈጣሪያቸውን እንዲያውቁ እርዷቸው
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሃይማኖት የሌላቸው ሰዎችን ልብ መንካት የምንችለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
  • የማስተማሪያ መሣሪያዎቻችንን በጥሩ ሁኔታ ተጠቀሙባቸው
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2018
  • እውነትን አስተምሩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018
  • ማስረጃውን መርምር
    ንቁ!—2021
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
mwb23 መስከረም ገጽ 13
አንዲት እህት ለአንዲት እስያዊት ሴት ስትመሠክር።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ሃይማኖት የሌላቸው ሰዎች ፈጣሪያቸውን እንዲያውቁ እርዷቸው

ሃይማኖት የሌላቸው ሰዎች ጥሩ ምላሽ እንደማይሰጡ በማሰብ ለእነሱ ከመስበክ ወደኋላ ብላችሁ ታውቃላችሁ? ከሆነ፣ አምላክ የለሾችን ጨምሮ ሃይማኖት የሌላቸው ብዙ ሰዎች የይሖዋ ምሥክሮች መሆን እንደቻሉ አስታውሱ። ብዙዎቹን ለዚህ ያበቃቸው አምላክ መኖሩን የሚያሳየውን ማስረጃ እንዲመረምሩ የተሰጣቸው ጥቂት ማበረታቻ ነው።—ሮም 1:20፤ 10:14

እምነት የለሽ ሰዎች እምነት ሊያዳብሩ እንደሚችሉ አስታውሱ!—ሃይማኖት የሌላቸው ሰዎች የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተለውን ጥያቄ ለመመለስ ሞክር፦

የቶማዞ ተሞክሮ ሃይማኖት ለሌላቸው ሰዎች ስለመስበክ አዎንታዊ አመለካከት ለመያዝ የሚረዳህ እንዴት ነው?

ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

አንድ ሰው በአምላክ እንደማያምን ከገለጸ በደግነትና በዘዴ ያዙት፤ እንዲሁም ስለ ጉዳዩ ያለውን አመለካከትና ስሜት ለመረዳት ጥረት አድርጉ። (2ጢሞ 2:24) ትኩረቱን ሊስቡ የሚችሉ ርዕሰ ጉዳዮችን አንሱ። ብዙዎች በፈጣሪ መኖር እንዲያምኑ ያደረጓቸውን ማስረጃዎች በተመለከተ ለመወያየት ፈቃደኛ ነው? ከሆነ፣ ለዚህ ዓላማ ተብለው የተዘጋጁትን ጽሑፎችና ቪዲዮዎች ተጠቀሙ። ሕይወት የተገኘው በፍጥረት ነው? እና የሕይወት አመጣጥ—መልስ የሚያሻቸው አምስት ጥያቄዎች የተባሉት ብሮሹሮች በማስተማሪያ መሣሪያዎቻችን ውስጥ ተካተዋል፤ ይህም በቀላሉ እንድናገኛቸው ይረዳናል።

በአምላክ ለማያምኑ ሰዎች ምሥራቹን ስለመስበክ ስታስቡ መጀመሪያ ላይ ፍርሃት ይሰማችሁ ይሆናል። ተሞክሮ ያለው አስፋፊ እንዲረዳችሁ ለምን አትጠይቁም? ይሖዋ በእሱ መኖር የማያምኑ ሰዎችን ጨምሮ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ ትክክለኛ የልብ ዝንባሌ ያላቸውን ሰዎች ለመርዳት ሊጠቀምብን እንደሚችል አስታውሱ።—ሥራ 13:48

“ሕይወት የተገኘው በፍጥረት ነው?” የሚለው ብሮሹር።
“የሕይወት አመጣጥ—መልስ የሚያሻቸው አምስት ጥያቄዎች” የሚለው ብሮሹር።
    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ