የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w20 ታኅሣሥ ገጽ 30
  • ታስታውሳለህ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ታስታውሳለህ?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሕይወት መራራ ሲሆን
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • በመንፈስ መሪነት በተቀናበረ መዝሙር ላይ ካሉ ምሳሌያዊ አገላለጾች የምናገኘው ትምህርት
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • ሳኦል መጀመሪያ ላይ ትሑትና ልኩን የሚያውቅ ሰው ነበር
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2022
  • ታማኝ ሰዎች ስእለታቸውን ይፈጽማሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2024
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020
w20 ታኅሣሥ ገጽ 30

ታስታውሳለህ?

በቅርቡ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች በደንብ አንብበሃቸዋል? እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

ለቅቡዓን ክርስቲያኖች ምን አመለካከት ሊኖረን ይገባል?

በእምነታቸው እናደንቃቸዋለን፤ ሆኖም ከሚገባው በላይ ትኩረት አንሰጣቸውም። ‘ሌሎችን ከመካብ’ እንቆጠባለን። (ይሁዳ 16) ቅቡዓኑን ስለ ተስፋቸው ተገቢ ያልሆኑ ጥያቄዎችን አንጠይቃቸውም።—w20.01 ከገጽ 28-29

ይሖዋ በግለሰብ ደረጃ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚመለከትህ የሚያሳይ ምን ማስረጃ አለ?

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ይሖዋ ከመወለድህ በፊት እንኳ አውቆሃል። እንዲሁም የምታቀርበውን ጸሎት ያዳምጣል። ይሖዋ ስሜትህንና ሐሳብህን ያውቃል፤ በተጨማሪም የምታደርገው ነገር ሊያስደስተው ወይም ሊያሳዝነው ይችላል። (1 ዜና 28:9፤ ምሳሌ 27:11) ከዚህም ሌላ ይሖዋ ወደ ራሱ ስቦሃል።​—w20.02 ገጽ 12

መናገር ያለብን መቼ ነው? መናገር የሌለብንስ መቼ ነው?

ስለ ይሖዋ መናገር ያስደስተናል። አንድ ሰው በአደገኛ ጎዳና ላይ እየተጓዘ እንደሆነ ብናይ በድፍረት መናገር አለብን። ሽማግሌዎች አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ምክር መስጠት ይኖርባቸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ሥራችን በታገደባቸው አገሮች ሥራው እንዴት እንደሚከናወን አንጠይቅም ወይም አንናገርም። እንዲሁም በሚስጥር መያዝ ያለባቸውን ጉዳዮች አንናገርም።​—w20.03 ከገጽ 20-21

በኢዩኤል ምዕራፍ 2 ላይ የተጠቀሱት አንበጦች በራእይ ምዕራፍ 9 ላይ ከተጠቀሱት አንበጦች የሚለዩት እንዴት ነው?

ኢዩኤል 2:20-29 አምላክ አንበጦቹን እንደሚያባርርና ላስከተሉት ጉዳት ማካካሻ ለመስጠት ቃል እንደገባ ይናገራል። ከዚያ በኋላ አምላክ መንፈሱን ያፈሳል። እነዚህ የትንቢቱ ገጽታዎች ባቢሎን እስራኤልን በወረረችበት ጊዜና ከዚያ በኋላ ባለው ዘመን ተፈጽመዋል። ራእይ 9:1-11 ደግሞ በአንበጣ የተመሰሉት ቅቡዓን ክርስቲያኖች፣ አምላክ በዚህ ክፉ ሥርዓት ላይ ያስተላለፈውን የፍርድ መልእክት እንደሚያውጁና የሥርዓቱን ደጋፊዎች እንደሚያሠቃዩ ይገልጻል።​—w20.04 ከገጽ 2-6

በዛሬው ጊዜ ‘የሰሜኑ ንጉሥ’ ማን ነው?

ሩሲያ እና አጋሮቿ ናቸው። እነዚህ ብሔራት ከአምላክ ሕዝቦች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው፤ በስብከቱ ሥራ ላይ እገዳ ጥለዋል፤ እንዲሁም ለይሖዋ ምሥክሮች ጥላቻ አሳይተዋል። የሰሜኑ ንጉሥ ከደቡቡ ንጉሥ ጋር እየተፎካከረ ነው።​—w20.05 ገጽ 13

“የመንፈስ ፍሬ” ገጽታዎች በገላትያ 5:22, 23 ላይ የተጠቀሱት ዘጠኝ ባሕርያት ብቻ ናቸው?

አይደሉም። መንፈስ ቅዱስ እንደ ጽድቅ ያሉ ሌሎች ግሩም ባሕርያትን ለማፍራትም ይረዳናል። (ኤፌ. 5:8, 9)​—w20.06 ገጽ 17

ኢንተርኔት ላይ ስለ ራሳችን የምናወጣቸው ነገሮች ምን ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ?

ኢንተርኔት ላይ የምናወጣቸው ነገሮች ጉራ እየነዛን እንዳለንና ትሕትና እንደጎደለን የሚያስመስሉ ሊሆኑ ይችላሉ።​—w20.07 ከገጽ 6-7

ክርስቲያኖች በሙያቸው ከተካኑ ዓሣ አጥማጆች ምን ትምህርት ማግኘት ይችላሉ?

ዓሣ አጥማጆች ሥራቸውን የሚያከናውኑት ዓሦች በሚገኙበት ቦታ እና ሰዓት ነው። ዓሣ አጥማጆች ለሥራቸው የሚያስፈልጋቸውን መሣሪያ አጠቃቀም በሚገባ ያውቃሉ። እንዲሁም ሁኔታዎች ቢለዋወጡም በድፍረት ሥራቸውን ያከናውናሉ። እኛም በአገልግሎት ስንካፈል ተመሳሳይ ነገር ማድረግ እንችላለን።​—w20.09 ገጽ 5

ጥናቶቻችን ለይሖዋ ያላቸው ፍቅር እንዲያድግ መርዳት የምንችለው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ እንዲያነቡና ባነበቡት ላይ እንዲያሰላስሉ ልናበረታታቸው እንችላለን። እንዲሁም እንዴት እንደሚጸልዩ ልናስተምራቸው እንችላለን።​—w20.11 ገጽ 4

“ሁሉም በክርስቶስ ሕያው ይሆናሉ” ከተባሉት መካከል እነማን ይገኙበታል?—1 ቆሮ. 15:22

ሐዋርያው ጳውሎስ ሁሉም ሰዎች ከሞት ይነሳሉ ማለቱ አልነበረም። ጳውሎስ “ሁሉም” ካላቸው መካከል ‘ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር ባላቸው አንድነት የተቀደሱት’ ቅቡዓን ክርስቲያኖች ይገኙበታል። (1 ቆሮ. 1:2፤ 15:18)​—w20.12 ከገጽ 5-6

ቅቡዓን ክርስቲያኖች ‘የመጨረሻው መለከት በሚነፋበት ወቅት በቅጽበተ ዓይን ከተለወጡ’ በኋላ ምን ሥራ ይጠብቃቸዋል?—1 ቆሮ. 15:51-53

ከክርስቶስ ጋር ሆነው ብሔራትን እንደ እረኛ በብረት በትር ይገዛሉ። (ራእይ 2:26, 27)​—w20.12 ከገጽ 12-13

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ