የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp21 ቁጥር 1 ገጽ 14-15
  • መጸለይህ ምን ጥቅም ያስገኝልሃል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መጸለይህ ምን ጥቅም ያስገኝልሃል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጸሎት እንዴት ሊጠቅምህ ይችላል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • በጸሎት አማካኝነት ከአምላክ ጋር ያለህን ዝምድና አጠናክር
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • ወደ አምላክ የመጸለይ ውድ መብት
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • በጸሎት አማካኝነት ወደ አምላክ ቅረብ
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
wp21 ቁጥር 1 ገጽ 14-15

መጸለይህ ምን ጥቅም ያስገኝልሃል?

ከባድ የጤና ችግር ያጋጠማት ፓሜላ የሕክምና እርዳታ ለማግኘት ጥረት ታደርግ ነበር። በተጨማሪም አምላክ ያለችበትን ከባድ ሁኔታ ለመወጣት ጥንካሬ እንዲሰጣት ትጸልይ ነበር። ታዲያ መጸለይዋ የረዳት እንዴት ነው?

ፓሜላ እንዲህ ብላለች፦ “የካንሰር ሕክምና በሚደረግልኝ ወቅት ብዙ ጊዜ ውስጤ በፍርሃት ይርድ ነበር። ወደ ይሖዋ ስጸልይ ግን የመረጋጋት ስሜት ስለሚሰማኝ አጥርቼ ማሰብ እችላለሁ። አሁንም ቢሆን ነጋ ጠባ ከሚያሠቃየኝ ሕመም ጋር እየታገልኩ ቢሆንም ጸሎት አዎንታዊ አመለካከት እንዲኖረኝ ይረዳኛል። ሰዎች ስለ ደህንነቴ ሲጠይቁኝ ‘ሕመሙ እንዳለ ቢሆንም ደስተኛ ነኝ!’ እላቸዋለሁ።”

እርግጥ ወደ አምላክ ለመጸለይ ከባድ ሕመም እስኪይዘን መጠበቅ አያስፈልገንም። ይነስም ይብዛ ሁላችንም ተፈታታኝ ሁኔታዎች ስለሚያጋጥሙን እነዚህን ሁኔታዎች ለመወጣት እርዳታ ያስፈልገናል። ታዲያ ጸሎት በዚህ ረገድ ሊረዳን ይችላል?

መጽሐፍ ቅዱስ “ሸክምህን በይሖዋ ላይ ጣል፤ እሱም ይደግፍሃል። ጻድቁ እንዲወድቅ ፈጽሞ አይፈቅድም” ይላል። (መዝሙር 55:22) ይህ ሐሳብ ምንኛ የሚያጽናና ነው! ለመሆኑ ጸሎት የሚጠቅምህ እንዴት ነው? በተገቢው መንገድ ወደ አምላክ ከጸለይክ ያጋጠመህን ተፈታታኝ ሁኔታ ለመወጣት የሚያስፈልግህን ነገር ይሰጥሃል።—“ጸሎት ምን ለማግኘት ያስችልሃል?” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።

ጸሎት ምን ለማግኘት ያስችልሃል?

የአእምሮ ሰላም

ቀደም ሲል ከሥራ የተባረረው ሠራተኛ ፈገግ ብሎ በልበ ሙሉነት ሲራመድ

“ልመናችሁን ለአምላክ አቅርቡ፤ ከመረዳት ችሎታ ሁሉ በላይ የሆነው የአምላክ ሰላም በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት ልባችሁንና አእምሯችሁን ይጠብቃል።” (ፊልጵስዩስ 4:6, 7) ያስጨነቀህን ነገር ለአምላክ ስትነግረው እሱ እንድትረጋጋና ጥበብ የሚንጸባረቅበት እርምጃ እንድትወስድ ይረዳሃል።

ጥበብ

ከጸሎት መጽሐፍ ላይ ጸሎት እየደገመች የነበረችው ሴት ቤቷ መጽሐፍ ቅዱስ ስታነብ

“ከእናንተ መካከል ጥበብ የጎደለው ሰው ካለ አምላክን ያለማሰለስ ይለምን፤ አምላክ ማንንም ሳይነቅፍ ለሁሉም በልግስና ይሰጣልና፤ ይህም ሰው ይሰጠዋል።” (ያዕቆብ 1:5) ውጥረት ውስጥ ስንሆን ትክክለኛ ውሳኔ ማድረግ ይከብደን ይሆናል። ጥበብ ለማግኘት ስትጸልይ አምላክ በቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ጠቃሚ መመሪያዎችን እንድታስታውስ ሊረዳህ ይችላል።

ብርታትና ማጽናኛ

ቀደም ሲል ሆስፒታል የነበሩት ባልና ሚስት መናፈሻ ውስጥ አብረው ሲሄዱ። ባልየው ከዘራ ይዛ የምትራመድ ሚስቱን ደገፍ አድርጓታል

“ኃይልን በሚሰጠኝ በእሱ አማካኝነት ለሁሉም ነገር የሚሆን ብርታት አለኝ።” (ፊልጵስዩስ 4:13) ይሖዋ ሁሉን ቻይ አምላክ ስለሆነ ያጋጠመህን ተፈታታኝ ሁኔታ ለመቋቋም ወይም ፈተናውን ለማለፍ የሚያስፈልግህን ብርታት ሊሰጥህ ይችላል። (ኢሳይያስ 40:29) በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ ይሖዋን “የመጽናናት ሁሉ አምላክ” በማለት ይጠራዋል። “እሱ በሚደርስብን መከራ ሁሉ ያጽናናናል።”—2 ቆሮንቶስ 1:3, 4

አንተስ ከዚህ ዝግጅት ተጠቃሚ መሆን ትፈልጋለህ?

ይሖዋ ወደ እሱ እንድትጸልይ አያስገድድህም። ከዚህ ይልቅ ወደ እሱ እንድትጸልይ ፍቅራዊ ግብዣ አቅርቦልሃል። (ኤርምያስ 29:11, 12) ይሁንና ከዚህ በፊት ጸልየህ መልስ እንዳላገኘህ የሚሰማህ ከሆነስ? ልታዝን ወይም ተስፋ ልትቆርጥ አይገባም። አፍቃሪ ወላጆች ልጆቻቸውን የሚረዱት ልጆቹ በጠበቁበት መንገድ ወይም በጠየቁበት ሰዓት ላይሆን ይችላል። ምናልባት ወላጆቹ የተሻለ መፍትሔ ይኖራቸው ይሆናል። ስለ አንድ ነገር ግን እርግጠኞች ነን፦ አፍቃሪ ወላጆች ልጆቻቸውን መርዳታቸው አይቀርም።

በተመሳሳይም ከየትኛውም ወላጅ ይበልጥ አፍቃሪ የሆነው አባታችን ይሖዋ አንተን ሊረዳህ ይፈልጋል። እስካሁን የተመለከትናቸውን መመሪያዎች በሚገባ ከመረመርክና ሥራ ላይ ለማዋል ጥረት ካደረግክ አምላክ ጸሎትህን ከሁሉ በተሻለ መንገድ ይመልስልሃል!—መዝሙር 34:15፤ ማቴዎስ 7:7-11

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ