የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp21 ቁጥር 3 ገጽ 6-8
  • ትምህርትና ገንዘብ ሕይወትን አስተማማኝ ለማድረግ ይረዳሉ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትምህርትና ገንዘብ ሕይወትን አስተማማኝ ለማድረግ ይረዳሉ?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ብዙዎች የሚያደርጉት ምርጫ
  • ውጤቱ ምን ያሳያል?
  • የይሖዋ ምሥክሮች ለትምህርት ምን አመለካከት አላቸው?
    ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች
  • ወላጆች—ልጆቻችሁ ወደፊት ምን እንዲሆኑ ትፈልጋላችሁ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • አስተማማኝ የወደፊት ሕይወት—የሁሉም ሰው ምኞት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
  • የወደፊት ሕይወትን አስተማማኝ ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
wp21 ቁጥር 3 ገጽ 6-8
ሁለት ወጣት ሴቶች ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ወደሚማሩበት ክፍል ሲሄዱ

ትምህርትና ገንዘብ ሕይወትን አስተማማኝ ለማድረግ ይረዳሉ?

ብዙዎች፣ የተማሩና ሀብታም የሆኑ ሰዎች ሕይወታቸው አስተማማኝ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ዩኒቨርሲቲ ገብቶ መማር ጎበዝ ሠራተኛና የተሻለ ዜጋ ለመሆን እንዲሁም ጥሩ የቤተሰብ ሕይወት ለመምራት እንደሚረዳ ያምናሉ። በተጨማሪም ጥሩ ትምህርት፣ የተሻለ ክፍያ የሚያስገኝ ሥራ ለመያዝ እንደሚያስችልና ከፍ ያለ ገቢ ያላቸው ሰዎች ደስተኛ እንደሚሆኑ ያስባሉ።

ብዙዎች የሚያደርጉት ምርጫ

በቻይና የሚኖረው ጃንግ ቸን የሰጠውን አስተያየት እንመልከት። እንዲህ ብሏል፦ “ከድህነት መላቀቅ የምችልበት ብቸኛው መንገድ የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ መያዝ እንደሆነ ይሰማኝ ነበር። ‘አስደሳችና አርኪ ሕይወት ለመምራት ከፍተኛ ደሞዝ የሚያስገኝ ሥራ መያዝ አለብኝ’ የሚል አስተሳሰብ ነበረኝ።”

ብዙዎች የወደፊት ሕይወታቸውን አስተማማኝ ለማድረግ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ገብተው መማር ይፈልጋሉ፤ ምናልባትም በእነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር ሲሉ ወደ ሌላ አገር ሊሄዱ ይችላሉ። በኮቪድ-19 ምክንያት ዓለም አቀፍ ጉዞ ማድረግ ከባድ እስከሆነበት ጊዜ ድረስ ይህ ነገር በጣም የተለመደ ሆኖ ነበር። የኢኮኖሚ ትብብርና እድገት ድርጅት (OECD) በ2012 ባወጣው ሪፖርት ላይ እንደገለጸው “ወደ ውጭ አገር ሄደው ከሚማሩ ተማሪዎች መካከል 52 በመቶ የሚሆኑት የእስያ ተወላጆች ናቸው።”

ብዙውን ጊዜ ወላጆች ልጆቻቸውን ውጭ አገር ወዳለ ዩኒቨርሲቲ ልከው ለማስተማር ሲሉ ከፍተኛ መሥዋዕትነት ይከፍላሉ። በታይዋን የሚኖረው ቺሺያንግ እንዲህ ብሏል፦ “ወላጆቼ ሀብታሞች አይደሉም፤ ግን እኔን ጨምሮ አራት ልጆቻቸውን ዩናይትድ ስቴትስ ወዳለ ኮሌጅ ልከው አስተምረዋል።” እንደ ሌሎች በርካታ ቤተሰቦች ሁሉ የቺሺያንግ ቤተሰቦችም ለዚህ የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን ሲሉ ከባድ ዕዳ ውስጥ ተዘፍቀዋል።

ውጤቱ ምን ያሳያል?

ከሁለቱ ሴቶች አንዷ ምሽት ላይ ድካምና ውጥረት ተሰምቷት ኮምፒውተሯ ፊት ለፊት ተቀምጣለች

ከፍተኛ ትምህርት በመከታተልና ሀብት በማሳደድ ላይ ያተኮረ ሕይወት የመሩ በርካታ ሰዎች የኋላ ኋላ ለብስጭት ተዳርገዋል

ትምህርት ሕይወትን የሚያሻሽልባቸው አንዳንድ መንገዶች ሊኖሩ ይችላሉ፤ አንዳንድ ጊዜ ግን ሰዎች ትምህርታቸውን ከጨረሱ በኋላ የጠበቁትን ዓይነት ሕይወት አያገኙም። ለምሳሌ ያህል፣ ብዙ ሰዎች ለዓመታት መሥዋዕትነት ከፍለውና ከፍተኛ ዕዳ ውስጥ ተዘፍቀው ትምህርታቸውን ቢያጠናቅቁም የፈለጉትን ሥራ ማግኘት አልቻሉም። ሬቸል ሙዪ የተባለች ጋዜጠኛ በሲንጋፖር ቢዝነስ ታይምስ ላይ ያወጣችው ሪፖርት እንዲህ ይላል፦ “ከተመረቁ በኋላ ሥራ አጥተው የሚቀመጡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ አሳሳቢ ሆኗል።” በታይዋን የሚኖር ጂየንጂየ የተባለ የዶክትሬት ምሩቅ “ብዙዎች ከተመረቁበት ትምህርት ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው ሥራ ለመያዝ ተገደዋል” በማለት ተናግሯል።

አንዳንዶች በፈለጉት የሙያ መስክ ሥራ ቢያገኙም ሕይወታቸው ያሰቡትን ያህል አስተማማኝ አልሆነም። በታይላንድ የሚኖረው ናይረን ዩናይትድ ኪንግደም ሄዶ የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን አጠናቆ ከተመለሰ በኋላ በተማረበት መስክ ሥራ አገኘ። እንዲህ ብሏል፦ “እንደጠበቅኩት በዲግሪ መመረቄ ከፍተኛ ደሞዝ የሚያስገኝ ሥራ እንድይዝ ረድቶኛል። ግን ይህን ደሞዝ ለማግኘት ስል ብዙ ሰዓት መሥራት ይጠበቅብኝ ነበር፤ የሥራ ጫናውም ከባድ ነበር። ከጊዜ በኋላ ድርጅቱ እኔን ጨምሮ አብዛኞቹን ሠራተኞቹን ከሥራ ቀነሰ። ይህ አጋጣሚ የትኛውም ሥራ ቢሆን አስተማማኝ እንዳልሆነ እንድገነዘብ አድርጎኛል።”

ሀብታም የሆኑ ወይም የተደላደለ የሚባል ሕይወት የሚመሩ ሰዎችም እንኳ የቤተሰብ ወይም የጤና ችግር ያጋጥማቸዋል፤ የገንዘብ ጉዳይም ያስጨንቃቸዋል። በጃፓን የሚኖረው ካትሱቶሺ እንዲህ ሲል በሐቀኝነት ተናግሯል፦ “ብዙ ገንዘብ የነበረኝ ቢሆንም ፉክክሩና ሰዎች በምቀኝነት ተነሳስተው የሚያደርሱብኝ በደል አማሮኝ ነበር።” በቬትናም የምትኖር ላም የተባለች ሴት ደግሞ እንዲህ ብላለች፦ “ብዙ ሰዎች ጥሩ ደሞዝ የሚያስገኝ ሥራ መያዛቸው የወደፊት ሕይወታቸውን አስተማማኝ ለማድረግ እንደሚረዳቸው ይሰማቸዋል። እውነታው ግን ከዚህ ተቃራኒ ነው፤ እንዲህ ያለ ሥራ ያላቸው ሰዎች ብዙ ይጨነቃሉ፣ ጤንነታቸው ይጎዳል እንዲሁም ስሜታዊ ቀውስና የመንፈስ ጭንቀት ያጋጥማቸዋል።”

ትምህርትና ገንዘብ ብቻ በቂ ያልሆነው ለምንድን ነው?

ሰዎች ራሳቸውንም ሆነ ቤተሰባቸውን ለማስተዳደር መሠረታዊ የሆነ ትምህርትና ገንዘብ እንደሚያስፈልጋቸው አይካድም። ሆኖም እነዚህ ነገሮች በራሳቸው የወደፊት ሕይወታችንን አስተማማኝ ሊያደርጉልን አይችሉም። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው? እስቲ የፈጣሪ ቃል ምን እንደሚል ተመልከት።

ከፍተኛ ትምህርት ሁሌ ለስኬት ያበቃል ማለት አይደለም።

“ፈጣኖች በውድድር ሁልጊዜ አያሸንፉም፤ . . . አስተዋዮች ሁልጊዜ ሀብት አያገኙም፤ እውቀት ያላቸው ሰዎችም ሁልጊዜ ስኬታማ አይሆኑም፤ ምክንያቱም ሁሉም መጥፎ ጊዜና ያልተጠበቁ ክስተቶች ያጋጥሟቸዋል።”—መክብብ 9:11

ስኬታማ ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁ ሰዎች በአብዛኛው ስኬታማ ሳይሆኑ ይቀራሉ፤ እንቅፋት የሚሆኑባቸው ነገሮች ብዙውን ጊዜ ከእነሱ ቁጥጥር ውጭ ናቸው። በጣም የተማሩ የሚባሉ ሰዎችም እንኳ በኢኮኖሚ አለመረጋጋት፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ ባለው የፍትሕ መጓደልና በጭፍን ጥላቻ ምክንያት የፈለጉትን ነገር ማድረግ ሳይችሉ ይቀራሉ።

ሀብት ዘላቂ ላይሆን ይችላል።

“ሀብት ለማግኘት አትልፋ። ይህን ትተህ በማስተዋል ተመላለስ። ዓይንህን ስትጥልበት በዚያ አታገኘውም፤ የንስር ዓይነት ክንፎች አውጥቶ ወደ ሰማይ ይበርራልና።”—ምሳሌ 23:4, 5

ገንዘብ የሚያስገኘው የትኛውም ዓይነት ጥበቃ ጊዜያዊ ነው። አንድ ሰው ዕድሜ ልኩን ለፍቶ ያጠራቀመውን ገንዘብ በአንድ ሌሊት ሊያጣው ይችላል። እንደ መሬት መንቀጥቀጥ፣ ሰደድ እሳትና አውሎ ነፋስ ባሉ የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ሰዎች ቤት ንብረታቸውን አጥተው ባዶ እጃቸውን የሚቀሩበት ጊዜ አለ።

ገንዘብ በአብዛኛው ችግር አስከትሎ ይመጣል።

“ባለጸጋ ሰው ያለው ብዙ ሀብት . . . እንቅልፍ ይነሳዋል።”—መክብብ 5:12

በሆንግ ኮንግ የሚኖረው ፍራንክሊን ይህ ሐሳብ እውነት መሆኑን በገዛ ሕይወቱ ተመልክቷል። ከፍተኛ ትምህርት የተማረ ከመሆኑም ሌላ ጥሩ ደሞዝ የሚያስገኝ ሥራ ነበረው። በኋላም እድገት አግኝቶ ሥራ አስኪያጅ ሆነ። ፍራንክሊን እንዲህ ብሏል፦ ‘ሥራው የሚያስከትልብኝ ውጥረት ጤንነቴን ያቃውሰው ጀመር። በጣም ከመጨነቄ የተነሳ እንቅልፍ አልነበረኝም።’ በመጨረሻም በዚህ ሁኔታ መቀጠል እንደማይችል ተገነዘበ። እንዲህ ሲል ተናግሯል፦ ‘“ይህን ሁሉ የማደርገው ለምን ብዬ ነው?” እያልኩ ራሴን መጠየቅ ጀመርኩ። ይህም ስለ ሕይወት ዓላማ ይበልጥ እንዳስብ አደረገኝ።’

“ሀብት ለማግኘት አትልፋ።”—ምሳሌ 23:4

ፍራንክሊንን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በሕይወት ውስጥ ከፍተኛ ትምህርትን ከመከታተልና ሀብት ከማሳደድ የበለጠ ቦታ የሚሰጣቸው ነገሮች እንዳሉ ተገንዝበዋል። አንዳንዶች ቁሳዊ ሀብትን በማሳደድ ላይ ከማተኮር ይልቅ ጥሩ ሰው በመሆንና ሌሎችን በመርዳት የወደፊት ሕይወታቸውን የተሻለ ማድረግ እንደሚችሉ ይሰማቸዋል። ሆኖም እንዲህ ያለውን አኗኗር መከተል የወደፊት ሕይወትን አስተማማኝ ለማድረግ ይረዳል? ቀጣዩ ርዕስ የዚህን ጥያቄ መልስ ይዟል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ