የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp21 ቁጥር 3 ገጽ 3
  • አስተማማኝ የወደፊት ሕይወት—የሁሉም ሰው ምኞት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አስተማማኝ የወደፊት ሕይወት—የሁሉም ሰው ምኞት
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መግቢያ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
  • የወደፊት ሕይወትን አስተማማኝ ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
  • ጥሩ ሰው መሆን ብቻ የወደፊት ሕይወትን አስተማማኝ ያደርጋል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
  • ትምህርትና ገንዘብ ሕይወትን አስተማማኝ ለማድረግ ይረዳሉ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
wp21 ቁጥር 3 ገጽ 3
ትንሽ ልጃቸውን ያቀፉ ወላጆች አበባ ያወጣን አንድ ዛፍ እየተመለከቱ ሲያደንቁ

አስተማማኝ የወደፊት ሕይወት—የሁሉም ሰው ምኞት

የወደፊት ሕይወትህ ምን ዓይነት እንዲሆን ትፈልጋለህ? አብዛኞቹ ሰዎች ለራሳቸውም ሆነ ለቤተሰባቸው ደስታ፣ ጤናና ሰላም የሞላበት እንዲሁም የተደላደለ ሕይወት ይመኛሉ፤ አንተም እንዲህ ዓይነት ሕይወት እንደምትፈልግ ጥርጥር የለውም።

ይሁንና በርካታ ሰዎች የሚመኙትን ዓይነት ሕይወት የማግኘታቸው ጉዳይ ያጠራጥራቸዋል። እንደ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ያሉ ድንገተኛና ያልተጠበቁ ክስተቶች የማኅበረሰቡን ኑሮ ሲያመሰቃቅሉ፣ ኢኮኖሚውን ሲያናጉና ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ሲጥሉ ተመልከተዋል። በዚህም ምክንያት አስተማማኝ የወደፊት ሕይወት የሕልም እንጀራ እንደሆነ ይሰማቸዋል።

ይህ ሁኔታ የፈጠረው ግራ መጋባት ሰዎች አስተማማኝ ሕይወት ይሰጡናል ብለው የሚያስቧቸውን ነገሮች ሁሉ ወደመፈለግ ዞር እንዲሉ አድርጓቸዋል። አንዳንዶች እንደ ዕድል ወይም ዕጣ ፋንታ ያሉ የማይታዩ ኃይሎች ሕይወታቸውን እንዲቆጣጠሩት ይፈቅዳሉ። ብዙዎች ደግሞ ትምህርት እና ሀብት አስተማማኝ ሕይወት ለማግኘት እንደሚረዷቸው በማሰብ እነዚህን ነገሮች ያሳድዳሉ። አስተማማኝ ሕይወት ለመምራት የሚያስፈልገው ጥሩ ሰው መሆን ብቻ ነው ብለው የሚያስቡ ሰዎችም አሉ።

እነዚህ አማራጮች የምትፈልገውን ዓይነት ሕይወት ለማግኘት የሚረዱህ ይመስልሃል? መልሱን ለማግኘት የሚከተሉትን ጥያቄዎች መመርመር ያስፈልግሃል፦

  • የወደፊት ሕይወትህ የተመካው በምን ላይ ነው?

  • ትምህርትና ገንዘብ ሕይወትን አስተማማኝ ለማድረግ ይረዳሉ?

  • ጥሩ ሰው መሆንህ ብቻ የወደፊት ሕይወትህን አስተማማኝ ያደርገዋል?

  • የወደፊት ሕይወትህን በተመለከተ አስተማማኝ መመሪያ ማግኘት የምትችለው ከየት ነው?

ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ እንድታገኝ ሊረዳህ ይችላል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ