የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp21 ቁጥር 3 ገጽ 9-11
  • ጥሩ ሰው መሆን ብቻ የወደፊት ሕይወትን አስተማማኝ ያደርጋል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጥሩ ሰው መሆን ብቻ የወደፊት ሕይወትን አስተማማኝ ያደርጋል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ብዙዎች የሚከተሉት የሕይወት ጎዳና
  • ውጤቱ ምን ያሳያል?
  • አስተማማኝ የወደፊት ሕይወት—የሁሉም ሰው ምኞት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
  • የወደፊት ሕይወትን አስተማማኝ ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
  • መግቢያ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
  • ‘የዋሆች ምድርን ይወርሳሉ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2018
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
wp21 ቁጥር 3 ገጽ 9-11
አንዲት ሴት አውቶቡስ ውስጥ ለአንዲት በዕድሜ የገፉ ሴት ወንበሯን ስትለቅ

ጥሩ ሰው መሆን ብቻ የወደፊት ሕይወትን አስተማማኝ ያደርጋል?

ብዙ ሰዎች ጥሩና መልካም ሥነ ምግባር ያለው ሰው መሆን የወደፊት ሕይወትን አስተማማኝ ለማድረግ እንደሚረዳ ያምናሉ፤ እንዲህ ዓይነቱ አስተሳሰብ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት የዘለቀ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ በሩቅ ምሥራቅ የሚኖሩ ሰዎች ፈላስፋና መምህር የሆነው ኮንፊሽየስ (551-479 ዓ.ዓ.) ለተናገረው “ሌሎች እንዲያደርጉባችሁ የማትፈልጉትን ነገር እናንተም አታድርጉባቸው” ለሚለው ሐሳብ ከፍተኛ አክብሮት አላቸው።a

ብዙዎች የሚከተሉት የሕይወት ጎዳና

በዛሬው ጊዜም ብዙ ሰዎች ጥሩ ሥነ ምግባር ማሳየት የወደፊት ሕይወትን አስተማማኝ ለማድረግ ይረዳል ብለው ያምናሉ። ሰው አክባሪና ጨዋ ለመሆን፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ ያላቸውን ሚና በሚገባ ለመወጣትና ጥሩ ሕሊና ለመያዝ ጥረት ያደርጋሉ። ሊን የተባለች በቬትናም የምትኖር ሴት “ሐቀኛና ቅን ከሆንኩ የኋላ ኋላ እባረካለሁ ብዬ አምን ነበር” ብላለች።

ይህችው ሴት ለተቸገሩና መኖሪያ ለሌላቸው ምግብ ስትሰጥ

አንዳንዶች መልካም ለማድረግ የሚነሳሱት በሃይማኖታቸው ምክንያት ነው። በታይዋን የሚኖር ሹ-ዩን የተባለ ሰው እንዲህ ብሏል፦ “አንድ ሰው ከሞተ በኋላ ለዘላለም እንዲደሰት ወይም እንዲሠቃይ የሚያደርገው በሕይወት ሳለ የሠራው ሥራ እንደሆነ ተምሬያለሁ።”

ውጤቱ ምን ያሳያል?

ሴትየዋ ማታ ላይ ትንሽ ልጇን አቅፋ፤ ፊቷ ላይ ሐዘንና ድካም ይነበባል

ለሌሎች መልካም ማድረጋችን ብዙ ጥቅም እንደሚያስገኝልን አይካድም። ሆኖም ለሌሎች መልካም ለማድረግ ከልባቸው የሚጥሩ በርካታ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ የጠበቁትን ውጤት እንደማያገኙ ተመልክተዋል። በሆንግ ኮንግ የምትኖር ሺዮ ፒንግ የተባለች ሴት “‘መልካም የሚያደርጉ ሰዎች በምላሹ ሁሌም ይባረካሉ’ የሚለው አባባል እውነት እንዳልሆነ በራሴ ሕይወት አይቻለሁ” ብላለች። አክላም እንዲህ ስትል ተናግራለች፦ “ቤተሰቤን ለመንከባከብና ጥሩ ለማድረግ የቻልኩትን ሁሉ እጥር ነበር። ሆኖም ትዳሬ ፈረሰ፤ ባለቤቴ እኔንና ልጄን ትቶን ሄደ።”

ብዙዎች፣ ሃይማኖተኛ የሚባሉ ሰዎችም እንኳ መጥፎ ነገር እንደሚያደርጉ አስተውለዋል። ኤትስኮ የተባለች በጃፓን የምትኖር ሴት “አንድ የሃይማኖት ድርጅት ውስጥ ገብቼ የወጣቶችን እንቅስቃሴ እስከማደራጀት ደርሼ ነበር” ብላለች። አክላም “በዚያ ውስጥ ያለውን የሥነ ምግባር ዝቅጠትና የሥልጣን ሽኩቻ እንዲሁም ገንዘብ ለማጭበርበር የሚያደርጉትን ጥረት ሳይ በጣም ደነገጥኩ” በማለት ተናግራለች።

“ቤተሰቤን ለመንከባከብና ጥሩ ለማድረግ የቻልኩትን ሁሉ እጥር ነበር። ሆኖም ትዳሬ ፈረሰ፤ ባለቤቴ እኔንና ልጄን ትቶን ሄደ።”—ሺዮ ፒንግ፣ ሆንግ ኮንግ

አንዳንድ ሃይማኖተኛ ሰዎች መልካም ነገር ቢያደርጉም በምላሹ ምንም ጥሩ ነገር ባለማግኘታቸው ተስፋ ቆርጠዋል። በቬትናም የምትኖር ቫን የተባለች ሴት እንዲህ ተሰምቷታል። እንዲህ ብላለች፦ “በየዕለቱ ፍራፍሬ፣ አበባና ምግብ ገዝቼ ለሞቱ ዘመዶቼ መሥዋዕት አቀርብ ነበር። እንዲህ ማድረጌ በረከት ያስገኝልኛል ብዬ አምን ነበር። ለበርካታ ዓመታት መልካም ሳደርግና ሃይማኖታዊ ሥርዓቶችን ስፈጽም የቆየሁ ቢሆንም ባለቤቴ በከባድ በሽታ ተያዘ። ከዚያም ሴት ልጄ ውጭ አገር ትምህርቷን እየተከታተለች ሳለ በለጋ ዕድሜዋ ሞተች።”

ጥሩ ሰው መሆን ብቻ በቂ ያልሆነው ለምንድን ነው?

ጥሩ ሰው መሆን አስፈላጊ ቢሆንም ይህ በራሱ የወደፊት ሕይወታችንን አስተማማኝ አያደርግልንም። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው? እስቲ የፈጣሪ ቃል ምን እንደሚል ተመልከት።

ጥሩ ነገር የሚያደርጉት ሁሉም ሰዎች አይደሉም

“አንድ ኃጢአተኛ . . . ብዙ መልካም ነገርን ሊያጠፋ ይችላል።”—መክብብ 9:18

አንተ መልካም ለማድረግ ብትጥርም ራስ ወዳድ የሆኑ ሰዎች በሚያደርጉት ነገር የተነሳ ለአደጋ ልትጋለጥ ትችላለህ። ለምሳሌ ያህል፣ ወረርሽኝ በሚከሰትበት ወቅት ባለሥልጣናት የሚሰጡትን ምክር በመከተል አካላዊ ርቀትህን ለመጠበቅ ጥረት ታደርግ ይሆናል። አንዳንዶች ግን ይህን መመሪያ ለመከተል ፈቃደኛ ባይሆኑስ? የእነሱ ድርጊት ትክክል የሆነውን ነገር ለማድረግ የሚጥሩ ሰዎችን ጤንነት አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል።

ሰዎች ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር በተመለከተ የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ ሊደርሱ ይችላሉ

“ለሰው ትክክለኛ መስሎ የሚታይ መንገድ አለ፤ በመጨረሻ ግን ወደ ሞት ይመራል።”—ምሳሌ 14:12

በተደጋጋሚ እንደታየው፣ ብዙ ሰዎች ትክክል ነው ብለው ሲያደርጉ የቆዩት ነገር ስህተት እንደሆነ ከጊዜ በኋላ ተገንዝበዋል። አንድን ነገር ያደረጉት በቅን ልቦና ተነሳስተው መሆኑ ድርጊታቸው ከሚያስከትለው መዘዝ አይጠብቃቸውም።

በሕይወት ውስጥ ያልተጠበቁ ነገሮች ያጋጥማሉ

“ሕይወታችሁ ነገ ምን እንደሚሆን . . . አታውቁም።”—ያዕቆብ 4:14

አንድ ሰው የቱንም ያህል ጥሩ ቢሆን ሕይወቱ በአጭር ሊቀጭ ይችላል። ለምሳሌ ያህል፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት ራሳቸውን ሳይቆጥቡ ሌሎችን ይረዱ የነበሩ በርካታ ፈቃደኛ ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ሊቲንግ የተባለችን በቻይና የምትኖር ሴት ሁኔታ እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። ይህች ሴት አባቷን በመኪና አደጋ አጥታለች። እንዲህ ብላለች፦ “እንደ እሱ ያለ ደግ ሰው እንዲህ በአጭር መቀጨቱን ሳስበው ለማመን ይከብደኛል። አባቴ ትጉ ሠራተኛ፣ ትሑትና ቅን ነበር። ግን በመኪናው ውስጥ ከነበሩት መካከል የሞተው እሱ ብቻ ነው።”

ጥሩ ሰው መሆን ብቻ ሕይወታችንን አስተማማኝ የማያደርግልን ከሆነ ሕይወታችንን አስተማማኝ ሊያደርግልን የሚችለው ምንድን ነው? መልሱን ለማወቅ አስተማማኝ መመሪያ ያስፈልገናል፤ መመሪያው ደግሞ ጥያቄዎቻችንን ሊመልስልንና ስለ ወደፊቱ ጊዜ ትክክለኛ መረጃ ሊሰጠን የሚችል መሆን አለበት። እንዲህ ያለ መመሪያ ማግኘት የምንችለው ከየት ነው?

a ኮንፊሽየስ ያስተማረው ትምህርት በሰዎች ላይ ስላሳደረው ተጽዕኖ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን የሰው ዘር አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ (እንግሊዝኛ) የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 7፣ ከአንቀጽ 31-35 ተመልከት፤ መጽሐፉ www.jw.org ላይ ይገኛል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ