የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp18 ቁጥር 2 ገጽ 16
  • ‘የዋሆች ምድርን ይወርሳሉ’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘የዋሆች ምድርን ይወርሳሉ’
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2018
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እውነት ምን ጥቅም ያስገኝልሃል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2020
  • ወደ አምላክ መቅረብ ትችላለህ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2019
  • የወደፊት ሕይወትህ የተመካው በአንተ ምርጫ ላይ ነው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
  • ስለ ወደፊቱ ጊዜ ምን ይሰማሃል?
    ስለ ወደፊቱ ጊዜ ምን ይሰማሃል?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2018
wp18 ቁጥር 2 ገጽ 16
አንድ ቤተሰብ

‘የዋሆች ምድርን ይወርሳሉ’

አብዛኞቻችን ፍትሕ ሲዛባና ክፉዎች ትክክል የሆነውን ማድረግ በሚፈልጉ ሰዎች ላይ ግፍ ሲፈጽሙ ተመልክተናል። የፍትሕ መዛባትና ክፋት የማይኖሩበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው መዝሙር 37 የዚህን ጥያቄ መልስ የሚሰጠን ሲሆን ለዘመናችን የሚጠቅም መመሪያም ይዟል። መዝሙር 37 ቀጥሎ ለቀረቡት ጥያቄዎች የሚሰጠውን መልስ ልብ በል፦

  • ሰዎች ግፍ ሲፈጽሙብን ምን ማድረግ ይኖርብናል?—ቁጥር 1, 2

  • ክፉ ሰዎች መጨረሻቸው ምን ይሆናል?—ቁጥር 10

  • ትክክል የሆነውን የሚያደርጉ ሰዎች ወደፊት ምን ይጠብቃቸዋል?—ቁጥር 11, 29

  • ዛሬ ከእያንዳንዳችን ምን ይጠበቃል?—ቁጥር 34

በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተጻፈው መዝሙር 37 ‘ይሖዋን ተስፋ የሚያደርጉና መንገዱን የሚከተሉ’ ሰዎች ብሩሕ ተስፋ እንደሚጠብቃቸው ይናገራል። የይሖዋ ምሥክሮች መጽሐፍ ቅዱስን እንድታጠና ሊረዱ ይችላሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናትህ አንተም ሆንክ ቤተሰብህ አስተማማኝ የወደፊት ተስፋ እንዲኖራችሁ ይረዳችኋል።

አምላክ ስለሰጠው አስተማማኝ ተስፋ ይበልጥ ማወቅ ከፈለግህ በይሖዋ ምሥክሮች በተዘጋጀው ለዘላለም በደስታ ኑር! በተባለው ብሮሹር አማካኝነት መጽሐፍ ቅዱስን እንድትማር እንጋብዝሃለን፤ ብሮሹሩ www.jw.org ላይም ይገኛል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ