የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp21 ቁጥር 3 ገጽ 15
  • የወደፊት ሕይወትህ የተመካው በአንተ ምርጫ ላይ ነው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የወደፊት ሕይወትህ የተመካው በአንተ ምርጫ ላይ ነው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ይሖዋን መውደድና ቃሉን መስማት የምንችለው እንዴት ነው?
  • የወደፊቱ ሕይወትህና የምታደርገው ምርጫ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2018
  • ወደ አምላክ መቅረብ ትችላለህ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2019
  • ‘የዋሆች ምድርን ይወርሳሉ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2018
  • መግቢያ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
wp21 ቁጥር 3 ገጽ 15
አንድ ሰው ካፌ ውስጥ ለጓደኛው ከስልኩ ላይ የሆነ ነገር ሲያሳየው

የወደፊት ሕይወትህ የተመካው በአንተ ምርጫ ላይ ነው

ከ3,500 ዓመታት ገደማ በፊት ይሖዋ አምላክ ለአገልጋዮቹ የወደፊት ሕይወታቸውን አስተማማኝ ለማድረግ ከእነሱ ምን እንደሚጠበቅ ነግሯቸዋል። እንዲህ ብሏቸዋል፦ “ሕይወትንና ሞትን፣ በረከትንና እርግማንን በፊታችሁ [አስቀምጫለሁ]፤ እንግዲህ አንተም ሆንክ ዘሮችህ በሕይወት እንድትኖሩ ሕይወትን ምረጥ።”—ዘዳግም 30:19

እነዚህ ሰዎች የወደፊት ተስፋቸው ብሩህ እንዲሆን ከፈለጉ ትክክለኛ ምርጫ ማድረግ ነበረባቸው። እኛም ተመሳሳይ ምርጫ ቀርቦልናል። መጽሐፍ ቅዱስ የወደፊቱን ጊዜ በተመለከተ ጥሩ ምርጫ ማድረግ የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ይናገራል፤ ‘አምላክህን ይሖዋን በመውደድ እና ቃሉን በመስማት ነው’ ይላል።—ዘዳግም 30:20

ይሖዋን መውደድና ቃሉን መስማት የምንችለው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስን ተማር፦ ይሖዋን ለመውደድ በቅድሚያ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስለ እሱ መማር ያስፈልግሃል። እንዲህ ስታደርግ ይሖዋ ለአንተ ከሁሉ የተሻለውን ነገር የሚመኝ አፍቃሪ አምላክ እንደሆነ ትገነዘባለህ። ወደ እሱ እንድትጸልይ ግብዣ አቅርቦልሃል፤ ‘ምክንያቱም እሱ ስለ አንተ ያስባል።’ (1 ጴጥሮስ 5:7) ወደ አምላክ ለመቅረብ ጥረት ካደረግክ ‘እሱም ወደ አንተ እንደሚቀርብ’ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።—ያዕቆብ 4:8

የተማርከውን ተግባራዊ አድርግ፦ አምላክን መስማት ማለት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን ጥበብ ያዘለ መመሪያ መከተል ማለት ነው። “እንዲህ ካደረግክ መንገድህ ይቃናልሃል፤ እንዲሁም ማንኛውንም ነገር በጥበብ ማከናወን ትችላለህ።”—ኢያሱ 1:8

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት jw.org የተባለውን ድረ ገጻችንን ተመልከት፤ ድረ ገጹ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ፣ ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችህ መልስ ማግኘት ወይም አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያስተምርህ መጠየቅ ትችላለህ።

ዛሬ በመጽሐፍ ቅዱስ ለመመራት መምረጥህ የወደፊት ሕይወትህን አስተማማኝ ያደርግልሃል!

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ