የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w22 ታኅሣሥ ገጽ 15
  • ታስታውሳለህ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ታስታውሳለህ?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “በአምላክ ቤት ሥራ ጣልቃ አትግቡ”
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • ይሖዋ እንዲጠቀምባችሁ ፍቀዱለት
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • የእምነት ባልንጀሮቻችሁን ፈጽሞ አትተዉአቸው
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • ለአዲሱ የአገልግሎት ዓመት የትኞቹን ግቦች አውጥታችኋል?
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
w22 ታኅሣሥ ገጽ 15

ታስታውሳለህ?

በዚህ ዓመት የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች በደንብ አንብበሃቸዋል? እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

ጊዜ መድበን ይሖዋን የምናነጋግረው፣ የምናዳምጠውና ስለ እሱ የምናስብ ከሆነ ምን ጥቅም እናገኛለን?

ጥሩ ውሳኔ የማድረግ ችሎታችን ይሻሻላል፤ የማስተማር ችሎታችን ይሻሻላል፤ እምነታችን ይበልጥ ይጠናከራል፤ እንዲሁም ለይሖዋ ያለን ፍቅር ይጨምራል።—w22.01 ገጽ 30-31

በይሖዋና በእሱ ወኪሎች ላይ እምነት ማዳበራችን የሚጠቅመን እንዴት ነው?

ሽማግሌዎች በሚሰጡን መመሪያዎችና በሚያደርጓቸው ውሳኔዎች ላይ ጥያቄ ባለማንሳት ከአሁኑ በአምላክ አሠራር ላይ እምነት ማዳበር ይኖርብናል። እንዲህ ካደረግን፣ በታላቁ መከራ ወቅት በእኛ አመለካከት እንግዳ የሆኑ ወይም ምክንያታዊ የማይመስሉ መመሪያዎች ቢሰጡን እንኳ ለመታዘዝ ዝግጁ እንሆናለን።—w22.02 ገጽ 4-6

መልአኩ ‘በገዢው ዘሩባቤል እጅ ላይ ስላለው ቱምቢ’ ለዘካርያስ የነገረው ለምንድን ነው? (ዘካ. 4:8-10)

ይህ ራእይ፣ ቤተ መቅደሱ ያን ያህል የሚያስደምም ባይሆንም እንኳ የግንባታ ሥራው እንደሚጠናቀቅና የይሖዋን መሥፈርት እንደሚያሟላ ለሕዝቡ ማረጋገጫ ሰጥቷቸዋል።—w22.03 ገጽ 16-17

‘በንግግራችን አርዓያ’ መሆን የምንችለው እንዴት ነው? (1 ጢሞ. 4:12)

በአገልግሎት ላይ ስንሆን በደግነትና በአክብሮት እንናገራለን፤ በስብሰባዎች ላይ ከልባችን እንዘምራለን እንዲሁም አዘውትረን ተሳትፎ እናደርጋለን፤ በተጨማሪም እውነቱን እንናገራለን፤ ሌሎችን እናንጻለን እንዲሁም ከመሳደብ እንቆጠባለን።—w22.04 ገጽ 6-9

በዳንኤል ምዕራፍ 7 ላይ የተጠቀሱት የአራቱ አውሬዎች (መንግሥታት) ገጽታዎች በራእይ 13:1, 2 ላይ በአንድ አውሬ ላይ የሚታዩት ለምንድን ነው?

በራእይ 13 ላይ የተጠቀሰው አውሬ እንደ ሮም ያለን አንድ መንግሥት ብቻ የሚያመለክት አይደለም። ከዚህ ይልቅ የሰው ልጆችን ሲያስተዳድሩ የቆዩትን ሁሉንም የፖለቲካ ኃይሎች ያመለክታል።—w22.05 ገጽ 9

በይሖዋ ፍትሕ እንደምንተማመን የምናሳይበት አንዱ ወሳኝ መንገድ ምንድን ነው?

አንድ ሰው ሲሰድበን፣ ስሜታችንን ሲጎዳው ወይም ሲበድለን ጉዳዩን ለይሖዋ በመተው ያደረብንን ቅሬታና ብስጭት ለማስወገድ ጥረት እናደርጋለን። ይሖዋ ኃጢአት ያስከተለውን ጉዳት በሙሉ ያስተካክላል።—w22.06 ገጽ 10-11

በስብሰባ ላይ ጸሎት የሚያቀርቡ ወንድሞች የትኞቹን ነገሮች ማስታወስ ይኖርባቸዋል?

ጉባኤውን ለመምከር ወይም ማስታወቂያ ለመናገር ጸሎትን መጠቀም ተገቢ አይደለም። በተለይም በስብሰባው መጀመሪያ ላይ ‘ቃላት ማብዛት’ አያስፈልግም። (ማቴ. 6:7)—w22.07 ገጽ 24-25

“ክፉ የሠሩ” ሰዎች “ለፍርድ ትንሣኤ” የሚወጡት በምን መንገድ ነው? (ዮሐ. 5:29)

ከመሞታቸው በፊት በሠሩት ሥራ መሠረት አሉታዊ ፍርድ ይሰጣቸዋል ማለት አይደለም። ከዚህ ይልቅ ከሞት ከተነሱ በኋላ በሚያሳዩት ባሕርይና ምግባር መሠረት ይገመገማሉ ማለት ነው።—w22.09 ገጽ 18

ጆሴፍ ራዘርፎርድ መስከረም 1922 በተደረገው ትልቅ ስብሰባ ላይ ምን ማሳሰቢያ ሰጠ?

በሴዳር ፖይንት፣ ኦሃዮ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በተካሄደው ትልቅ ስብሰባ ላይ “ንጉሡ በመግዛት ላይ ነው! እናንተ ደግሞ የእሱ አዋጅ ነጋሪዎች ናችሁ። ስለዚህ ንጉሡንና መንግሥቱን አስታውቁ፣ አስታውቁ፣ አስታውቁ!” በማለት ተናገረ።—w22.10 ገጽ 3-5

ኢሳይያስ ምዕራፍ 30 እንደሚናገረው አምላክ ለመጽናት የሚረዳን በየትኞቹ ሦስት መንገዶች ነው?

ይህ ምዕራፍ እንደሚገልጸው፣ አምላክ (1) ጸሎታችንን በጥሞና በማዳመጥና በመመለስ፣ (2) መመሪያ በመስጠት እንዲሁም (3) አሁንም ሆነ ወደፊት እኛን በመባረክ ይረዳናል።—w22.11 ገጽ 9

መዝሙር 37:10, 11, 29 በጥንት ዘመንም ሆነ ወደፊት ፍጻሜ እንዳለው በምን እናውቃለን?

የዳዊት ቃላት እስራኤል ውስጥ ለምሳሌ በሰለሞን የግዛት ዘመን የነበረውን የተትረፈረፈ በረከት ጥሩ አድርገው ይገልጻሉ። ኢየሱስ ወደፊት ስለሚመጣው ገነት በተናገረበት ወቅት ቁጥር 11⁠ን ጠቅሷል። (ማቴ. 5:5፤ ሉቃስ 23:43)—w22.12 ገጽ 8-10, 14

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ