የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp23 ቁጥር 1 ገጽ 10-11
  • 3 | ከመጽሐፍ ቅዱስ ባለታሪኮች የምናገኘው ትምህርት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • 3 | ከመጽሐፍ ቅዱስ ባለታሪኮች የምናገኘው ትምህርት
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2023
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ምን ማለት ነው?
  • የሚረዳን እንዴት ነው?
  • 2 | ‘ከቅዱሳን መጻሕፍት የምናገኘው መጽናኛ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2023
  • 4 | መጽሐፍ ቅዱስ ጠቃሚ ምክር ይሰጣል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2023
  • የጤና ችግር ቢኖርብኝ ምን ላድርግ? (ክፍል 3)
    የወጣቶች ጥያቄ
  • ስሜቴን መቆጣጠር የምችለው እንዴት ነው?
    የወጣቶች ጥያቄ
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2023
wp23 ቁጥር 1 ገጽ 10-11
ነቢዩ ሙሴ ተጨንቆ ወደ ሰማይ እየተመለከተ ወደ አምላክ ሲጸልይ።

3 | ከመጽሐፍ ቅዱስ ባለታሪኮች የምናገኘው ትምህርት

መጽሐፍ ቅዱስ . . . “እንደ እኛው ዓይነት ስሜት” የነበራቸውን ታማኝ ወንዶችና ሴቶች ታሪክ ይዟል።—ያዕቆብ 5:17

ምን ማለት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ የተለያየ ዓይነት ስሜት ያስተናገዱ በርካታ ወንዶችና ሴቶችን ታሪክ ይዟል። ከእነዚህ ታሪኮች መካከል የእኛ ዓይነት ስሜት ያጋጠመው ሰው እናገኝ ይሆናል።

የሚረዳን እንዴት ነው?

ሁላችንም ሌሎች ስሜታችንን እንዲረዱልን እንፈልጋለን። በተለይ ከአእምሮ ጤንነት ጋር የተያያዘ ችግር ሲያጋጥመን ስሜታችንን የሚረዳልን ሰው ይበልጥ እንፈልጋለን። የመጽሐፍ ቅዱስ ባለታሪኮች ያጋጠሟቸውን ነገሮች ስናነብ ከእኛ ጋር ተመሳሳይ የሆነ አስተሳሰብና ስሜት እንደነበራቸው እናስተውል ይሆናል። በዚህ ጊዜ፣ ከስሜታዊ ችግሮች ጋር የታገሉ ሌሎች ሰዎችም እንደነበሩ እንገነዘባለን፤ እንዲሁም ከጭንቀትና ከሚረብሹ ስሜቶች ጋር የምንታገለው እኛ ብቻ እንደሆንን አይሰማንም።

  • መጽሐፍ ቅዱስ፣ መውጫ ቀዳዳ እንዳጡ የተሰማቸው በርካታ ሰዎች የተናገሯቸውን ሐሳቦች ይዟል። ‘አሁንስ በቅቶኛል! ከአቅሜ በላይ ነው’ ብለህ ታውቃለህ? ሙሴ፣ ኤልያስና ዳዊት እንዲህ ዓይነት ስሜት ተሰምቷቸው ነበር።—ዘኁልቁ 11:14፤ 1 ነገሥት 19:4፤ መዝሙር 55:4

  • መጽሐፍ ቅዱስ ሐና የተባለች ሴት፣ ልጅ መውለድ ባለመቻሏ እንዲሁም ጣውንቷ በዚህ ምክንያት ታደርስባት በነበረው ዘለፋ የተነሳ “በጣም ተማርራ” እንደነበር ይናገራል።—1 ሳሙኤል 1:6, 10

  • መጽሐፍ ቅዱስ ኢዮብ የተባለን ሰው ታሪክ ይነግረናል፤ እኛም የእሱ ዓይነት ስሜት ይሰማን ይሆናል። ኢዮብ የእምነት ሰው ቢሆንም ከፍተኛ የስሜት ሥቃይ ስለደረሰበት በአንድ ወቅት “ሕይወቴን ተጸየፍኳት፤ በሕይወት መቀጠል አልፈልግም” ብሎ ነበር።—ኢዮብ 7:16

እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ባለታሪኮች አሉታዊ አስተሳሰባቸውን ማሸነፍ የቻሉት እንዴት እንደሆነ መማራችን ያለንበትን ሁኔታ ለመቋቋም የሚያስችል ብርታት ይሰጠናል።

መጽሐፍ ቅዱስ የረዳቸው እንዴት ነው? ኬቨን

የስሜት መዋዠቅ ያስከተለብኝ ጉዳት

ኬቨን ከሁለት ጓደኞቹ ጋር ቡና ሲጠጣ።

“በ40ዎቹ ዕድሜ መጨረሻ ላይ ሳለሁ የስሜት መዋዠቅ ችግር እንዳለብኝ በምርመራ ታወቀ። አንዳንድ ጊዜ በሕይወቴ ውስጥ የሚያጋጥመኝን ማንኛውንም ችግር ማሸነፍ እንደምችል ይሰማኛል። አንዳንድ ጊዜ ግን መኖር ምንም ዋጋ እንደሌለው ይሰማኛል።”

ከመጽሐፍ ቅዱስ ያገኘሁት እርዳታ

“ከመጽሐፍ ቅዱስ ባለታሪኮች መካከል ሐዋርያው ጴጥሮስ ከእኔ ጋር ተመሳሳይ ስሜት እንደነበረው ይሰማኛል። በፈጸማቸው ስህተቶች የተነሳ የከንቱነት ስሜት ተሰምቶት ነበር። ሆኖም በሐዘን ከመቆዘም ይልቅ ከሚያስቡለት ጓደኞቹ ጋር ጊዜ ለማሳለፍ መርጧል። እኔም የስሜት መዋዠቁ በሚያገረሽብኝ ጊዜ፣ ያሉብኝ ድክመቶች ተስፋ ስለሚያስቆርጡኝ የከንቱነት ስሜት ይሰማኛል። እኔም እንደ ጴጥሮስ ተስፋ እንዳልቆርጥ ከሚረዱኝ ጓደኞቼ ጋር ለመቀራረብ ጥረት ማድረግ እንዳለብኝ ተምሬያለሁ።

“በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው የንጉሥ ዳዊት ታሪክም በጣም ያጽናናኛል። ዳዊት ባለበት ሁኔታ የተነሳ በሐዘን የተዋጠበትና ቀደም ሲል በሠራቸው ስህተቶች የተጸጸተበት ጊዜ ነበር። እኔም በኋላ ላይ የሚጸጽቱኝን ነገሮች የምናገርበትና የማደርግበት ጊዜ ስላለ የእሱን ስሜት መረዳት እችላለሁ። ዳዊት በመዝሙር 51 ላይ የተናገራቸው ቃላት ያጽናኑኛል። በቁጥር 3 ላይ ዳዊት ‘መተላለፌን በሚገባ አውቃለሁና፤ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነው’ ብሎ ነበር። እነዚህ ቃላት በሐዘን በምዋጥበት ጊዜ የሚሰማኝን ስሜት ጥሩ አድርገው ይገልጻሉ፤ በዚህ ጊዜ ለራሴ አዎንታዊ አመለካከት መያዝ በጣም ይከብደኛል። ሆኖም ዳዊት በቁጥር 10 ላይ የተናገረውን ሐሳብም እጋራለሁ። ‘አምላክ ሆይ፣ ንጹሕ ልብ ፍጠርልኝ፤ በውስጤም ጽኑ የሆነ አዲስ መንፈስ አኑር’ ብሏል። እኔም አምላክ ለራሴ ያለኝን አመለካከት ለማስተካከል እንዲረዳኝ ተመሳሳይ ጸሎት አቀርባለሁ። ቁጥር 17ም በእጅጉ ያጽናናኛል። ‘አምላክ ሆይ፣ የተሰበረንና የተደቆሰን ልብ ችላ አትልም’ ይላል። ይህ ጥቅስ አምላክ እንደሚወደኝ ማረጋገጫ ይሰጠኛል።

“በመጽሐፍ ቅዱስ ባለታሪኮች ምሳሌ ላይ ማሰላሰሌ እንዲሁም አምላክ በሰጠኝ በረከቶች ላይ ማተኮሬ ለወደፊቱ ጊዜ ያለኝን ተስፋ ያጠናክርልኛል። የመጽሐፍ ቅዱስ ተስፋዎች እውን ሆነው እንዲታዩኝ ያደርጋል።”

ለተጨማሪ እርዳታ፦

በታኅሣሥ 2014 ንቁ! ላይ የሚገኘውን “የአእምሮ ሕመም—ምን ማወቅ ይኖርብሃል?” የሚለውን ርዕስ ከ​jw.org ላይ አንብብ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ