የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp23 ቁጥር 1 ገጽ 8-9
  • 2 | ‘ከቅዱሳን መጻሕፍት የምናገኘው መጽናኛ’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • 2 | ‘ከቅዱሳን መጻሕፍት የምናገኘው መጽናኛ’
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2023
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ምን ማለት ነው?
  • የሚረዳን እንዴት ነው?
  • የመንፈስ ጭንቀትና ወጣቶች—መንስኤውና መፍትሔው
    ንቁ!—2017
  • ‘የመጽናናት አምላክ’ የሚሰጠው እርዳታ
    ንቁ!—2009
  • አፍራሽ ስሜቶችን መቋቋም የምትችለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • በጣም የምጨነቀው ለምንድን ነው?
    ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2023
wp23 ቁጥር 1 ገጽ 8-9
አንድ አረጋዊ ሰው ከመጽሐፍ ቅዱስ ባነበበው ነገር ላይ ሲያሰላስል።

2 | ‘ከቅዱሳን መጻሕፍት የምናገኘው መጽናኛ’

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “በምናሳየው ጽናትና ከቅዱሳን መጻሕፍት በምናገኘው መጽናኛ ተስፋ ይኖረን ዘንድ ቀደም ብሎ የተጻፈው ነገር ሁሉ ለእኛ ትምህርት እንዲሆን ተጽፏል።”—ሮም 15:4

ምን ማለት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያጽናኑ ሐሳቦችን ይዟል፤ እነዚህ ሐሳቦች አፍራሽ አስተሳሰቦችን ለማሸነፍ የሚያስፈልገንን ብርታት ይሰጡናል። በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ፣ የስሜት ሥቃይ ያለፈ ታሪክ የሚሆንበት ጊዜ እንደሚመጣ ተስፋ ይሰጠናል።

የሚረዳን እንዴት ነው?

ሁላችንም አልፎ አልፎ ሐዘን ይሰማናል። ሆኖም ድባቴ ወይም ጭንቀት ያለባቸው ሰዎች በየዕለቱ ከማያቋርጥ የስሜት ሥቃይ ጋር መታገል ሊያስፈልጋቸው ይችላል። ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስ ሊረዳቸው የሚችለው እንዴት ነው?

  • በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉት አዎንታዊ ሐሳቦች በውስጣችን ያለውን አሉታዊ አስተሳሰብ ለማሸነፍ ይረዱናል። (ፊልጵስዩስ 4:8) መጽሐፍ ቅዱስ አእምሯችን በሚያጽናኑና በሚያረጋጉ ሐሳቦች እንዲሞላ ይረዳናል፤ ይህ ደግሞ ስሜታችንን ለመቆጣጠር ያስችለናል።—መዝሙር 94:18, 19

  • የከንቱነት ስሜት የሚሰማን ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ስሜት ለማሸነፍ ይረዳናል።—ሉቃስ 12:6, 7

  • ብቻችንን እንዳልሆንን እንዲሁም ፈጣሪያችን ስሜታችንን ሙሉ በሙሉ እንደሚረዳልን ዋስትና የሚሰጡን ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አሉ።—መዝሙር 34:18፤ 1 ዮሐንስ 3:19, 20

  • መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክ መጥፎ ትዝታዎችን በሙሉ እንደሚያስወግድ ተስፋ ይሰጠናል። (ኢሳይያስ 65:17፤ ራእይ 21:4) የሚረብሹ ሐሳቦችና ስሜቶች ሲመጡብን ይህ ተስፋ ለመጽናት የሚያስችል ብርታት ሊሰጠን ይችላል።

መጽሐፍ ቅዱስ የረዳቸው እንዴት ነው? ጄሲካ

ድባቴ ያደረሰብኝ ጉዳት

ጄሲካ የተገለጠ መጽሐፍ ቅዱስ በእጇ ይዛ እንቅልፍ ወስዷት።

“ሃያ አምስት ዓመት ሲሆነኝ በድንገት የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቼን ማከናወን ተሳነኝ፤ እንዲሁም ከባድ ድባቴa እንዳለብኝ በምርመራ ታወቀ። መጥፎ ትዝታዎች እየተመላለሱ ያሠቃዩኝ ጀመር። እዚህ ሁኔታ ውስጥ የገባሁት በሕይወቴ ውስጥ ያጋጠሙኝ መጥፎ ክስተቶች ባስከተሉት አሉታዊ አስተሳሰብ የተነሳ እንደሆነ ሐኪሞች ነገሩኝ። መድኃኒት መውሰድ እንዲሁም አሉታዊ አስተሳሰቦችን ለመለየትና ለማስተካከል ባለሙያ ማማከር ነበረብኝ።”

ከመጽሐፍ ቅዱስ ያገኘሁት እርዳታ

“ድባቴው በጣም ሲብስብኝ በከባድ ጭንቀት እዋጥ እንዲሁም እንቅልፍ አጣ ነበር። ብዙውን ጊዜ ሌሊት ላይ የሚረብሹ ሐሳቦች ወደ አእምሮዬ እየጎረፉ ያሠቃዩኝ ነበር። መዝሙር 94:19 እንደሚገልጸው በጭንቀት በምንዋጥበት ጊዜ አምላክ ሊያጽናናንና ሊያረጋጋን ይችላል። ስለዚህ በአልጋዬ አቅራቢያ መጽሐፍ ቅዱስና የሚያበረታቱ ጥቅሶችን የያዘ ማስታወሻ አስቀመጥኩ። እንቅልፍ አልወስድ ሲለኝ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በማንበብ ከአምላክ መጽናኛ ለማግኘት እሞክራለሁ።

“መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አምላክ ከምናውቀው ነገር ጋር የሚጻረሩ ሐሳቦችን እንድናፈርስ ያበረታታናል። ቀደም ሲል ምንም ዋጋ እንደሌለኝ፣ ማንም እንደማይወደኝ እንዲሁም እንደማልረባ ይሰማኝ ነበር። ሆኖም እንዲህ ያለው ሐሳብ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እንደሚጋጭ ተምሬያለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክ በግለሰብ ደረጃ የሚያስብልን አፍቃሪና ሩኅሩኅ አባታችን እንደሆነ ይናገራል። አሉታዊ አስተሳሰቤ እንዲቆጣጠረኝ ከመፍቀድ ይልቅ ቀስ በቀስ አስተሳሰቤን መቆጣጠር ቻልኩ። አምላክ እኔን በሚያየኝ መንገድ ራሴን ማየት ጀመርኩ። ይህም ለራሴ ያለኝን አሉታዊ አመለካከት ለማስተካከል በእጅጉ ረድቶኛል።

“መጥፎ ትዝታዎችና አፍራሽ አስተሳሰቦች ሙሉ በሙሉ የሚወገዱበትን ጊዜ በጉጉት እጠብቃለሁ። የአእምሮ ሕመም ያለፈ ታሪክ የሚሆንበት ጊዜ እንደሚመጣ ማወቄ አሁን ያለብኝን ችግር ለመቋቋም ብርታት ይሰጠኛል፤ እንዲሁም ከድባቴ ጋር የማደርገው ትግል የሚያቆምበትን ጊዜ በተስፋ እንድጠብቅ ይረዳኛል።”

a “ድባቴ” በመባል የሚታወቀው የአእምሮ ችግር “ድብርት” ወይም “የመንፈስ ጭንቀት” ተብሎም ይጠራል።

ለተጨማሪ እርዳታ፦

በሐምሌ 2009 ንቁ! ላይ የሚገኘውን “‘የመጽናናት አምላክ’ የሚሰጠው እርዳታ” የሚለውን ርዕስ ከ​jw.org ላይ አንብብ።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን የመዝሙር መጽሐፍ የድምፅ ቅጂ ከ​jw.org ላይ አዳምጥ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ