የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp23 ቁጥር 1 ገጽ 6-7
  • 1 | ጸሎት—‘የሚያስጨንቃችሁን ነገር ሁሉ በእሱ ላይ ጣሉ’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • 1 | ጸሎት—‘የሚያስጨንቃችሁን ነገር ሁሉ በእሱ ላይ ጣሉ’
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2023
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ምን ማለት ነው?
  • የሚረዳን እንዴት ነው?
  • የሚያስጨንቃችሁን ነገር ሁሉ በይሖዋ ላይ ጣሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
  • ጭንቀትን መቋቋም የምችለው እንዴት ነው?
    የወጣቶች ጥያቄ
  • ጭንቀትህን ሁሉ በይሖዋ ላይ ጣል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • በወንዶች ላይ የሚከሰት ጭንቀት—መጽሐፍ ቅዱስ ምን የመፍትሔ ሐሳብ ይሰጣል?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2023
wp23 ቁጥር 1 ገጽ 6-7
በጭንቀት የተዋጠ አንድ ወጣት እጁን ደረቱ ላይ አድርጎ ሲጸልይ።

1 | ጸሎት ‘የሚያስጨንቃችሁን ነገር ሁሉ በእሱ ላይ ጣሉ’

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “የሚያስጨንቃችሁንም ነገር ሁሉ [በአምላክ] ላይ ጣሉ፤ ምክንያቱም እሱ ስለ እናንተ ያስባል።”—1 ጴጥሮስ 5:7

ምን ማለት ነው?

ይሖዋ አምላክ ልባችንንና አእምሯችንን እንደ ሸክም ስለሚጫነን ስለ ማንኛውም ጉዳይ እንድናነጋግረው ጋብዞናል። (መዝሙር 55:22) ትንሽ ትልቅ ሳንል ስለ ማንኛውም ችግር መጸለይ እንችላለን። እኛን የሚያሳስበን ጉዳይ ሁሉ ይሖዋንም ያሳስበዋል። ወደ ይሖዋ መጸለይ የአእምሮ ሰላም ለማግኘት የሚረዳ ወሳኝ እርምጃ ነው።—ፊልጵስዩስ 4:6, 7

የሚረዳን እንዴት ነው?

የአእምሮ ጤና መቃወስ ሲያጋጥመን ብቻችንን እንደሆንን ሊሰማን ይችላል። ያለንበትን ሁኔታ ሌሎች ሰዎች ሙሉ በሙሉ ላይረዱልን ይችላሉ። (ምሳሌ 14:10) ሆኖም የሚሰማንን ሁሉ አውጥተን ለአምላክ በጸሎት ስንነግረው በደግነት ያዳምጠናል፤ ስሜታችንንም ይረዳልናል። ይሖዋ በትኩረት ይመለከተናል፤ የሚሰማንን ሥቃይና ያለብንን ትግል ይረዳል፤ እንዲሁም ስለሚያስጨንቀን ስለ ማንኛውም ነገር ወደ እሱ እንድንጸልይ ይፈልጋል።—2 ዜና መዋዕል 6:29, 30

ወደ ይሖዋ መጸለያችን እሱ እንደሚያስብልን ያለንን እምነት ያጠናክርልናል። “ጉስቁልናዬን አይተሃልና፤ በጭንቀት መዋጤን ታውቃለህ” በማለት የጸለየውን መዝሙራዊ ስሜት እንጋራለን። (መዝሙር 31:7) ይሖዋ ያለንበትን ሁኔታ በትኩረት እንደሚመለከት ማወቃችን በራሱ ያጋጠመንን አስቸጋሪ ሁኔታ በጽናት ለመቋቋም ይረዳናል። ሆኖም ይሖዋ ጭንቀታችንን በመመልከት ብቻ አይወሰንም። ያጋጠመንን ችግር ከማንም በተሻለ ይረዳል፤ እንዲሁም ከመጽሐፍ ቅዱስ ማጽናኛና ማበረታቻ እንድናገኝ ይረዳናል።

መጽሐፍ ቅዱስ የረዳቸው እንዴት ነው? ጁሊያን

ጭንቀት ያደረሰብኝ ጉዳት

ጁሊያን።

“ከጭንቀትና የማስበውን ነገር መቆጣጠር እንዲከብደኝ ከሚያደርግ የአእምሮ ሕመም ጋር እታገላለሁ። ያለምንም ምክንያት በጭንቀት እዋጣለሁ። ደህና ነኝ ስል ድንገት ጭንቀት ይይዘኛል። በተለይ ከሌሎች ሰዎች ጋር ስሆን እጨነቃለሁ። ሌሎች ለእኔ ያላቸው አመለካከት ከልክ በላይ ያሳስበኛል።

“ያለብኝን ትግል የሚያውቁ ሰዎች እኔን ለመርዳት ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ። እርግጥ አንዳንድ ጊዜ የሚናገሩት ነገር እንዳሰቡት ላይጠቅመኝ ይችላል። ግን በአሳቢነት ተነሳስተው የሚያደርጉትን ጥረት አደንቃለሁ።

“ባለብኝ ጭንቀት የአእምሮ ሕመም የተነሳ መጸለይ ይከብደኛል። ትኩረቴን ሰብስቤ ወደ ይሖዋ መጸለይ ብዙ ጥረት ይጠይቅብኛል። ሐሳቤ ከአንዱ ወደ ሌላው ቶሎ ቶሎ ስለሚዘል ሁሉ ነገር ይዘበራረቅብኛል። ሐሳቤ ከቁጥጥሬ ውጭ በሚሆንበት ጊዜ ስሜቴን በቃላት መግለጽ ይከብደኛል።”

ከመጽሐፍ ቅዱስ ያገኘሁት እርዳታ

“መጽሐፍ ቅዱስን ሳጠና እንደተረዳሁት ጸሎታችን በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ረጅም ወይም በሚገባ የተቀነባበረ መሆን አያስፈልገውም። አንዳንድ ጊዜ ስሜቴን በቃላት መግለጽ ሲከብደኝ ‘ይሖዋ፣ እባክህ እርዳኝ’ ብዬ አጭር ጸሎት አቀርባለሁ። በዚህ ጊዜም ቢሆን ይሖዋ ስሜቴን እንደሚረዳልኝና በሰዓቱ የሚያስፈልገኝን እርዳታ እንደሚሰጠኝ አስተውያለሁ። ከጸሎት በተጨማሪ የሕክምና እርዳታ ለማግኘት ጥረት አድርጌያለሁ። ከሁለቱም ምንጮች ያገኘሁት እርዳታ ሁኔታዬ በእጅጉ እንዲሻሻል ስላስቻለኝ አመስጋኝ ነኝ። የሰማዩን አባቴን ማነጋገርና የእሱን ፍቅራዊ ድጋፍ ማግኘት ምንም ዓይነት ጥረት ቢደረግለት የሚያስቆጭ አይደለም።”

ለወጣቶች የሚሆን እርዳታ

“የይሖዋ ወዳጅ ሁን—ሁልጊዜ ጸልይ” የሚለው ቪዲዮ።

ይሖዋ ጸሎትህን እንደሚሰማና እንደሚመልስልህ እርግጠኛ መሆን የምትችለው ለምን እንደሆነ ከ​jw.org ላይ ተማር።

የይሖዋ ወዳጅ ሁን—ሁልጊዜ ጸልይ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ