የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w23 ኅዳር ገጽ 31
  • ሁልዳ ግቧ ላይ ደረሰች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሁልዳ ግቧ ላይ ደረሰች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ከያዘው ዘገባ ጋር የሚስማማ ደረሰኝ
    ንቁ!—2009
  • መዳፋችን ውስጥ ያለ ቤተ መጻሕፍት
    የምታደርጉት መዋጮ ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው እንዴት ነው?
  • በፊጂ ደሴቶች የአምላክን መንግሥት ማስታወቅ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • “እንዲህ ያለ ፍቅር አግኝቼ አላውቅም”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
w23 ኅዳር ገጽ 31

ሁልዳ ግቧ ላይ ደረሰች

ኢንዶኔዥያ ውስጥ ሳንጊር ቤሳር በምትባል ትንሽ ደሴት ላይ ሦስት እህቶቻችን ይኖራሉ። ከተወሰኑ ዓመታት በፊት በባሕሩ ዳርቻ ላይ አብረው ይሠሩ ነበር። በደሴቲቱ ላይ የሚታወቁት በአገልግሎታቸው ማለትም ሰዎችን መጽሐፍ ቅዱስ በማስተማራቸው ነው። በዚያ ወቅት ግን ለየት ያለ ሥራ እየሠሩ ነበር።

ኢንዶኔዥያንና በዙሪያዋ ያሉትን አገሮች የሚያሳይ ካርታ። ትንሿ የሳንጊር ቤሳር ደሴት ጎላ ብላ ትታያለች።

በሰሜናዊ ኢንዶኔዥያ የሚገኘው የሳንጊር ቤሳር ደሴት

በመጀመሪያ ወደ ባሕሩ በመግባት ድንጋዮችን ይሰበስባሉ። አንዳንዶቹ ድንጋዮች እግር ኳስ ያክላሉ። ከዚያም ሴቶቹ በእንጨት ዱካ ላይ ተቀምጠው ድንጋዮቹን በመዶሻ ይፈረካክሷቸዋል። ቀጥሎም ጠጠሩን በፕላስቲክ ባልዲ ውስጥ ጨምረው ብዙ ደረጃ በመውጣት ወደሚኖሩበት አካባቢ ይወስዱታል። ከዚያም ጠጠሩን በትልቅ ከረጢት ውስጥ ከትተው መኪና ላይ ይጭኑታል፤ በመጨረሻም ጠጠሩ ለመንገድ ሥራ ይውላል።

ሁልዳ የባሕሩ ዳርቻ ላይ ድንጋይ ስትሰበስብ

ከእነዚህ እህቶች አንዷ ሁልዳ ትባላለች። ያለችበት ሁኔታ ከሌሎቹ እህቶች ይበልጥ በዚህ ሥራ ረዘም ያለ ሰዓት እንድታሳልፍ ይፈቅድላታል። የምታገኘውን ገንዘብ የምትጠቀምበት ቤተሰቧን ለማስተዳደር ነው። በዚህ ወቅት የምትሠራው ግን ተጨማሪ ግብ በአእምሮዋ ይዛ ነበር። JW Library አፕሊኬሽንን ለመጠቀም ታብሌት መግዛት ፈልጋ ነበር። ሁልዳ አፕሊኬሽኑ ላይ የሚገኙት ቪዲዮዎችና ሌሎች ጽሑፎች ለአገልግሎት እንደሚጠቅሟትና መጽሐፍ ቅዱስን በተሻለ መንገድ ለመረዳት እንደሚያግዟት ተሰምቷት ነበር።

ሁልዳ ለአንድ ወር ተኩል ያህል በየቀኑ ጠዋት ጠዋት ለሁለት ሰዓት ይህን ሥራ ታከናውን ነበር፤ በዚህ መንገድ አንድ አነስተኛ የጭነት መኪና የሚሞላ ድንጋይ መከስከስ ቻለች። በስተ መጨረሻ ታብሌት ለመግዛት የሚበቃ ገንዘብ አገኘች።

ሁልዳ ታብሌቷን ይዛ

ሁልዳ እንዲህ ብላለች፦ “ለረጅም ሰዓት ድንጋይ በመከስከሴ ሰውነቴ ደክሞና ዝሎ ነበር፤ ሆኖም አዲሱ ታብሌት በአገልግሎት ይበልጥ ውጤታማ ለመሆንና ለስብሰባዎች በቀላሉ ለመዘጋጀት እንዳስቻለኝ ሳይ ሕመሜንና ድካሜን ወዲያውኑ ረሳሁት።” በተጨማሪም ወረርሽኙ በጀመረበት ወቅት ሁሉም የጉባኤ እንቅስቃሴዎች የሚካሄዱት በቪዲዮ ኮንፈረንስ ስለነበር ታብሌቷ በእጅጉ እንደጠቀማት ተናግራለች። ሁልዳ ግቧ ላይ በመድረሷ በጣም ተደስተናል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ