የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w24 ሰኔ ገጽ 19
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2024
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የይሖዋ ሕዝቦች ለእውነተኛው አምልኮ ይቀናሉ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
  • ‘የዋሆች ምድርን ይወርሳሉ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2018
  • ‘እሱ ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም’ የሐዋርያት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ይሖዋ ስሜት አለው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2024
w24 ሰኔ ገጽ 19

የአንባቢያን ጥያቄዎች

በመዝሙር 12:7 ላይ “ትጋርዳቸዋለህ” የተባሉት በቁጥር 5 ላይ የተጠቀሱት ‘የተጎሳቆሉ ሰዎች’ ናቸው ወይስ በቁጥር 6 ላይ የተጠቀሱት የይሖዋ “ቃላት” (የ1954 ትርጉም)?

አውዱ እንደሚጠቁመው ጥቅሱ የሚናገረው ስለ ሰዎች ነው።

መዝሙር 12:1-4 “ከሰው ልጆች መካከል ታማኞች ጠፍተዋል” የሚል ሐሳብ ይዟል። ቀጥሎም መዝሙር 12:5-7 እንዲህ ይላል፦

“‘የተጎሳቆሉት ሰዎች በመጨቆናቸው፣

ድሆችም በመቃተታቸው፣

እርምጃ ለመውሰድ እነሳለሁ’ ይላል ይሖዋ።

‘በንቀት ዓይን ከሚመለከቷቸው ሁሉ እታደጋቸዋለሁ።’

የይሖዋ ቃል የጠራ ነው፤

ከሸክላ በተሠራ ምድጃ እንደተጣራ ብር ሰባት ጊዜ የነጠረ ነው።

ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ትጋርዳቸዋለህ፤

እያንዳንዳቸውን ከዚህ ትውልድ ለዘላለም ትጠብቃቸዋለህ።”

ቁጥር 5 አምላክ ለተጨቆኑ ሰዎች ምን እንደሚያደርግላቸው ይናገራል፤ ያድናቸዋል።

ቁጥር 6 ደግሞ ‘የይሖዋ ቃል እንደተጣራ ብር የጠራ እንደሆነ’ ይናገራል። ቀናተኛ የሆኑ ክርስቲያኖች የዳዊትን ስሜት ሙሉ በሙሉ ይጋራሉ።—መዝ. 18:30፤ 119:140

አሁን ደግሞ ቀጣዩን ቁጥር ማለትም መዝሙር 12:7⁠ን እንመልከት፤ “ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ትጋርዳቸዋለህ፤ እያንዳንዳቸውን ከዚህ ትውልድ ለዘላለም ትጠብቃቸዋለህ” ይላል። ይህ ጥቅስ የሚናገረው ስለ እነማን ነው?

ከዚህ በፊት ያለው ጥቅስ የሚናገረው ስለ ይሖዋ ቃል ስለሆነ አንዳንድ ሰዎች ይሖዋ ‘የሚጋርደው’ ቃሉን ነው የሚል መደምደሚያ ላይ ሊደርሱ ይችላሉ። እውነት ነው፣ ተቃዋሚዎች መጽሐፍ ቅዱስን ለማገድም ሆነ ለማጥፋት ጥረት ቢያደርጉም ይሖዋ ጥበቃ አድርጎለታል።—ኢሳ. 40:8፤ 1 ጴጥ. 1:25

ሆኖም በቁጥር 5 ላይ የተጠቀሰው ሐሳብም እውነት እንደሆነ እናውቃለን። ከዚህ ቀደም ይሖዋ ለተጎሳቆሉና ለተጨቆኑ ሰዎች እርዳታ አድርጓል እንዲሁም ታድጓቸዋል፤ ወደፊትም እንዲሁ ያደርጋል።—ኢዮብ 36:15፤ መዝ. 6:4፤ 31:1, 2፤ 54:7፤ 145:20

ታዲያ ቁጥር 7 የሚናገረው ስለ እነማን ነው?

የመዝሙሩ አጠቃላይ ይዘት እንደሚጠቁመው ቁጥር 7 የሚናገረው ስለ ሰዎች ነው።

መዝሙር 12:1 ክፉዎች ስለሚዋሿቸው “ታማኞች” ሁኔታ ይናገራል። ቀጥሎም ይሖዋ አምላክ አንደበታቸውን አላግባብ በሚጠቀሙ ሰዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የሚጠቁም ሐሳብ እናገኛለን። ይህ መዝሙር የይሖዋ ቃል የጠራ ስለሆነ እሱ ለሕዝቦቹ ሲል እርምጃ እንደሚወስድ መተማመን እንደምንችል ዋስትና ይሰጠናል።

ስለዚህ ቁጥር 7 የሚናገረው ክፉዎች ያጎሳቆሏቸውን ሰዎች ይሖዋ እንደሚጋርዳቸውና እንደሚጠብቃቸው ነው።

ይህ ጥቅስ “ትጋርዳቸዋለህ” እንዲሁም “ትጠብቃቸዋለህ” ተብሎ የተተረጎመው ጥንታዊውን የማሶሬቶች የዕብራይስጥ ጽሑፍ መሠረት በማድረግ ነው። የግሪክኛው ሰብዓ ሊቃናት ቁጥር 7 ላይ “ትጋርደናለህ” እንዲሁም “ትጠብቀናለህ” የሚሉ ቃላትን ይጠቀማል፤ ይህም ጥቅሱ የሚናገረው ስለተጨቆኑና ስለተጎሳቆሉ ታማኝ ሰዎች መሆኑን ይጠቁማል። በመጨረሻም፣ ቁጥር 7 “እያንዳንዳቸውን ከዚህ ትውልድ ለዘላለም ትጠብቃቸዋለህ” ይላል፤ ይህም ታማኞች ብልሹ ምግባርን ከሚያስፋፉ ሰዎች ጥበቃ እንደሚያገኙ ያመለክታል። (መዝ. 12:7, 8) በአረማይኩ ታርገም ላይ ቁጥር 7 የተተረጎመው እንዲህ ተብሎ ነው፦ “ጌታ ሆይ፣ አንተ ጻድቃንን ትጠብቃለህ፤ ከዚህ ክፉ ትውልድ ለዘላለም ትጋርዳቸዋለህ።” ይህም መዝሙር 12:7 የሚናገረው ስለ አምላክ ቃላት እንዳልሆነ የሚያሳይ ተጨማሪ ማስረጃ ነው።

ስለዚህ ይህ ጥቅስ፣ አምላክ ለታማኝ ሰዎች ሲል እርምጃ እንደሚወስድ ተስፋ የሚሰጥ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ