መግቢያ
ጦርነትና ግጭት በሌለበት ዓለም ውስጥ ለመኖር ትጓጓለህ? ብዙዎች እንዲህ ያለውን ዓለም ለማየት ቢጓጉም ይህ እውን ሊሆን እንደማይችል ይሰማቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ፣ የሰው ልጆች ጦርነትን ለማስወገድ ያደረጉት ጥረት ያልተሳካው ለምን እንደሆነ ይነግረናል። በተጨማሪም ዓለም አቀፋዊ ሰላም በቅርቡ እውን እንደሚሆን እርግጠኛ መሆን የምንችለው ለምን እንደሆነ ያብራራል።
በዚህ መጽሔት ውስጥ “ጦርነት” እና “ግጭት” የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት መሣሪያ የታጠቁ ቡድኖች ፖለቲካዊ አጀንዳቸውን ለማሳካት ሲሉ የሚያደርጉትን ውጊያ ነው። በዚህ መጽሔት ውስጥ የተጠቀሱት የአንዳንዶቹ ሰዎች ስም ተቀይሯል።