የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp25 ቁጥር 1 ገጽ 6-8
  • ጦርነትን እና ግጭትን በሰው አቅም ማስወገድ ይቻላል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጦርነትን እና ግጭትን በሰው አቅም ማስወገድ ይቻላል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2025
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የኢኮኖሚ እድገት
  • ዲፕሎማሲ
  • የጦር መሣሪያ ቅነሳ
  • የመንግሥታት ኅብረት
  • ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ለዓለም ሰላም ያመጡ ይሆን?
    ንቁ!—2004
  • ሰዎች በሰላም መኖር ያቃታቸው ለምን ይሆን?—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • ውጊያው የሚያበቃው መቼ ነው?—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • ዘላቂ ሰላም ሊያመጣ የሚችለው ማን ነው?
    ንቁ!—1996
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2025
wp25 ቁጥር 1 ገጽ 6-8

ጦርነትን እና ግጭትን በሰው አቅም ማስወገድ ይቻላል?

ሰዎች የሚዋጉት በተለያየ ምክንያት ነው። አንዳንዶች የሚዋጉት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ወይም ማኅበራዊ ለውጥ ለማምጣት ነው። ሌሎች ደግሞ የሚዋጉት መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ለመቆጣጠር ነው። የበርካታ ግጭቶች መንስኤ ለረጅም ጊዜ የዘለቀ የዘር ወይም የሃይማኖት ልዩነት ነው። ሰዎች እንዲህ ያሉትን ጦርነቶች ለማስቆምና ሰላም ለማስፈን ምን ጥረት እያደረጉ ነው? ጥረታቸውስ ይሳካ ይሆን?

በግንባታ ላይ ባለ ሕንፃ ውስጥ ያሉ የግንባታ ሠራተኞችን የሚያሳይ የተቀደደ ፎቶግራፍ።

Drazen_/E+ via Getty Images

የኢኮኖሚ እድገት

ግብ፦ የሰዎችን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል። ይህም ለብዙ ግጭቶች መንስኤ የሆነውን ኢፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል ለማስወገድ ወይም ለመቀነስ ያስችላል።

እንቅፋት፦ ይህን ለማሳካት መንግሥታት ገንዘብ የሚያወጡበትን መንገድ ማስተካከል ይጠበቅባቸዋል። በ2022 ለሰላም ግንባታና ሰላም ለማስከበር በዓለም ዙሪያ 34.1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደወጣ ይገመታል። ሆኖም በዚያው ዓመት ከጦርነት ጋር ለተያያዙ ወጪዎች ከዋለው ገንዘብ ጋር ሲወዳደር ይህ 0.4 በመቶ ብቻ ነው።

“ግጭቶች ያስከተሉትን ጉዳት ለማስተካከል የምናወጣው ገንዘብና ሀብት ግጭቶችን ለማስቀረትና ሰላም ለመገንባት ከምናወጣው ገንዘብ በእጅጉ ይበልጣል።”—አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? የዓለም መንግሥታትና ተቋማት ድሆችን ሊረዱ ቢችሉም መቼም ቢሆን ድህነትን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ አይችሉም።—ዘዳግም 15:11፤ ማቴዎስ 26:11

እየተጨባበጡ ያሉ ሁለት እጆችን የሚያሳይ የተቀደደ ፎቶግራፍ።

ዲፕሎማሲ

ግብ፦ በውይይትና በድርድር ሁለቱንም ወገኖች የሚጠቅም ስምምነት ላይ በመድረስ ግጭቶች እንዳይደርሱ መከላከል ወይም በሰላማዊ መንገድ መፍታት።

እንቅፋት፦ አንዱ ወገን ወይም ሁለቱም ወገኖች ለመደራደር ወይም ለመስማማት ፈቃደኛ ላይሆኑ ይችላሉ። ደግሞም የሰላም ስምምነቶች በቀላሉ ይፈርሳሉ።

“ዲፕሎማሲ ስኬታማ የሚሆነው ሁልጊዜ አይደለም። አንድን ጦርነት ለማቆም በድርድር የሚደረስበት ስምምነት በጣም ኢፍትሐዊ ከመሆኑ የተነሳ ለሌላ ግጭት በር ሊከፍት ይችላል።”—ሬመንድ ስሚዝ፣ የአሜሪካ ዲፕሎማሲ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? ሰዎች ‘ሰላምን መፈለግ’ አለባቸው። (መዝሙር 34:14) ሆኖም በዛሬው ጊዜ ያሉ ብዙ ሰዎች “ታማኝ ያልሆኑ፣ . . . ለመስማማት ፈቃደኞች ያልሆኑ፣ . . . ከዳተኞች” ናቸው። (2 ጢሞቴዎስ 3:1-4) አንዳንድ የፖለቲካ መሪዎች ግጭቶችን የመፍታት ልባዊ ፍላጎት ቢኖራቸውም እንኳ የእነዚህ ባሕርያት መስፋፋት እንቅፋት ይሆንባቸዋል።

የተሰባበረ ጠመንጃ የሚያሳይ የተቀደደ ፎቶግራፍ።

የጦር መሣሪያ ቅነሳ

ግብ፦ የጦር መሣሪያዎችን በተለይም የኑክሌር፣ የኬሚካልና የባዮሎጂካል መሣሪያዎችን መቀነስ ወይም ማስወገድ።

እንቅፋት፦ ብዙውን ጊዜ ብሔራት ኃይላቸው እንዳይዳከም ወይም ለጥቃት ተጋላጭ እንዳይሆኑ ስለሚፈሩ የጦር መሣሪያቸውን ለመቀነስ ፈቃደኛ አይሆኑም። የጦር መሣሪያዎችን ማስወገድ የግጭቶቹ መንስኤ የሆነውን ችግር አይፈታም።

“በቀዝቃዛው ጦርነት ማብቂያ ላይ ብዙዎቹ መንግሥታት የጦር መሣሪያዎቻቸውን ለመቀነስ የገቡትን ቃል አልፈጸሙም፤ ለምሳሌ አደገኛ ሁኔታዎችን ለመቀነስ የሚያስችሉ ተግባራዊ እርምጃዎችን ለመውሰድ፣ በአገራት መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ፣ በስተ መጨረሻም ይበልጥ ሰላማዊና ከስጋት ነፃ የሆነ ዓለም ለመፍጠር የተደረገው ስምምነት አልተሳካም።”—የጋራ ዕጣችንን አስተማማኝ ማድረግ፦ የመሣሪያ ቅነሳ አጀንዳ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? ሰዎች የጦር መሣሪያቸውን ማስወገድና ‘ሰይፋቸውን ማረሻ ለማድረግ መቀጥቀጥ’ አለባቸው። (ኢሳይያስ 2:4) ሆኖም ይህ ብቻውን በቂ አይደለም፤ ምክንያቱም ዓመፀኝነት የሚመነጨው ከሰዎች ልብ ነው።—ማቴዎስ 15:19

በጠረጴዛ ዙሪያ የተቀመጡ የአገር መሪዎችን የሚያሳይ የተቀደደ ፎቶግራፍ። ሁሉም ተመሳሳይ ሰነድ ላይ እየፈረሙ ነው።

የመንግሥታት ኅብረት

ግብ፦ ብሔራት በጠላቶቻቸው ላይ የጋራ እርምጃ ለመውሰድ ስምምነት ያደርጋሉ። በመሠረተ ሐሳብ ደረጃ፣ አንድ አገር በርካታ ብሔራት ተባብረው የአጸፋ ምላሽ እንደሚሰጡት ካወቀ ጥቃት ለመሰንዘር አይነሳሳም።

እንቅፋት፦ የአጸፋ ስጋት መኖሩ ለሰላም ዋስትና አይሆንም። አንዳንድ ብሔራት ስምምነታቸውን ላያከብሩ ይችላሉ፤ በተጨማሪም በጠላቶቻቸው ላይ እርምጃ የሚወስዱት መቼና እንዴት እንደሆነ ላይስማሙ ይችላሉ።

“የመንግሥታት ቃል ኪዳን ማኅበር ስምምነትም ሆነ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር መንግሥታት ኅብረት እንዲፈጥሩ የሚያበረታቱ ቢሆንም እነዚህ ጥረቶች ሙሉ በሙሉ ከሽፈዋል።”—ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? ብዙውን ጊዜ፣ ተባብሮ መሥራት የተሻለ ውጤት ያስገኛል። (መክብብ 4:12) ሆኖም ሰብዓዊ ተቋማት ዘላቂ ሰላምና ደህንነት ሊያመጡ አይችሉም። “ማዳን ስለማይችሉ በመሪዎች ወይም በማንኛውም ፍጡር አትተማመኑ። እነርሱ በሚሞቱበት ጊዜ ወደ ዐፈር ይመለሳሉ፤ በዚያኑ ቀን ዕቅዳቸው ሁሉ ይጠፋል።”—መዝሙር 146:3, 4 የ1980 ትርጉም

ብዙዎች ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም አሁንም ጦርነት መቅሰፍት ሆኖብናል።

ዓለማችን ይበልጥ ሰላማዊ ቦታ ሆናለች?

አንዳንዶች ዓለማችን ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ በአሁኑ ወቅት ሰላማዊ እንደሆነች ይናገራሉ። በዛሬው ጊዜ የሚካሄዱ ጦርነቶች በርዝመታቸውም ሆነ በገዳይነታቸው የተሻሉ እንደሆኑ እንዲሁም ካለፉት መቶ ዘመናት ጋር ሲወዳደር በጦርነት የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር በአንጻራዊ ሁኔታ አነስተኛ እንደሆነ ይናገራሉ። ሌሎች ግን በዚህ ሐሳብ አይስማሙም፤ እንዲሁም ይህን ሐሳብ ለመደገፍ እንደ ማስረጃ ሆነው በሚቀርቡት አኃዛዊ መረጃዎች ላይ እምነት የላቸውም።

ሰዎች ምንም አሉ ምን፣ በዛሬው ጊዜ ጥቂት የማይባለው የዓለም ሕዝብ በጦርነት የተነሳ ቀጥተኛ ጉዳት እየደረሰበት ነው፤ በተዘዋዋሪ መንገድ ደግሞ ጦርነት ሁላችንንም እየጎዳን ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ