ለጥናት የሚረዱ ሐሳቦች
ከኅዳግ ማጣቀሻዎች ጥቅም ማግኘት
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት የኅዳግ ማጣቀሻዎች ተጨማሪ መረጃ የያዙ ጥቅሶችን በመጠቆም መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በእርሱ የሚስማማ መሆኑን ያሳያሉ። አንድ ቃል የኅዳግ ማጣቀሻዎች ካሉት ከቃሉ አጠገብ ትንሽዬ ፊደል ይኖራል። የታተመውን መጽሐፍ ቅዱስ ስትጠቀም ተዛማጅ ጥቅሶችን ለማግኘት ያንኑ ፊደል በገጹ መሃል ላይ ፈልገው። jw.org ወይም JW ላይብረሪ አፕሊኬሽን ስትጠቀም ደግሞ ማጣቀሻው ላይ ያሉትን ጥቅሶች ለማግኘት ፊደሏን ተጫናት።
የኅዳግ ማጣቀሻዎች የሚከተሉትን መረጃዎች ለማግኘት ሊረዱህ ይችላሉ፦
ተመሳሳይ ዘገባ፦ ማጣቀሻው ያው ክንውን የተመዘገበበትን ሌላ ጥቅስ ይጠቁምሃል። ለምሳሌ 2 ሳሙኤል 24:1ን እና 1 ዜና መዋዕል 21:1ን ተመልከት።
ምንጭ፦ ማጣቀሻው አንድ ሐረግ ወይም አገላለጽ የተወሰደበትን ጥቅስ ያሳያል። ለምሳሌ ማቴዎስ 4:4ን እና ዘዳግም 8:3ን ተመልከት።
የትንቢት ፍጻሜ፦ ማጣቀሻው ትንቢቱን ከፍጻሜው ጋር ያዛምዳል። ለምሳሌ ማቴዎስ 21:5ን እና ዘካርያስ 9:9ን ተመልከት።