የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwfq ርዕስ 32
  • የይሖዋ ምሥክሮች በብሉይ ኪዳን ያምናሉ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የይሖዋ ምሥክሮች በብሉይ ኪዳን ያምናሉ?
  • ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ክርስቲያኖች ብሉይ ኪዳንም ሆነ አዲስ ኪዳን የሚያስፈልጋቸው ለምንድን ነው?
  • “ለትምህርታችን ተጽፎአል”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • የይሖዋ ምሥክሮች ብሉይ ኪዳንን ይቀበላሉ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አሁንም ይጠቅማሉ?
    ንቁ!—2010
  • “ብሉይ ኪዳን” ወይስ “የዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች”?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
ለተጨማሪ መረጃ
ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች
ijwfq ርዕስ 32

የይሖዋ ምሥክሮች በብሉይ ኪዳን ያምናሉ?

አዎ። የይሖዋ ምሥክሮች መላው መጽሐፍ ቅዱስ ‘በአምላክ መንፈስ መሪነት እንደተጻፈና ጠቃሚ’ እንደሆነ ያምናሉ። (2 ጢሞቴዎስ 3:16) ይህ ደግሞ በተለምዶ ብሉይ ኪዳን እና አዲስ ኪዳን ተብለው የሚጠሩትን ክፍሎች ይጨምራል። አብዛኛውን ጊዜ፣ የይሖዋ ምሥክሮች እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍትና የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት በማለት ይጠሯቸዋል። ይህም አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ጊዜ እንዳለፈባቸው ወይም እንደማይጠቅሙ አድርገን እንደማንመለከታቸው ያሳያል።

ክርስቲያኖች ብሉይ ኪዳንም ሆነ አዲስ ኪዳን የሚያስፈልጋቸው ለምንድን ነው?

ክርስቲያኑ ሐዋርያው ጳውሎስ በመንፈስ መሪነት “ቀደም ብሎ የተጻፈው ነገር ሁሉ ለእኛ ትምህርት እንዲሆን ተጽፏል” ብሏል። (ሮም 15:4) በመሆኑም በዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ አስፈላጊ መረጃ እናገኛለን። ለምሳሌ ያህል፣ መጻሕፍቱ ጠቃሚ የሆኑ ታሪኮችንና ምክሮችን ይዘዋል።

  • ጠቃሚ የሆኑ ታሪኮች። የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ስለ ፍጥረት እንዲሁም የሰው ዘር በኃጢአት የወደቀው እንዴት እንደሆነ የሚገልጽ ዝርዝር ዘገባ ይዘዋል። ይህ መረጃ ባይኖረን ኖሮ ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ ማግኘት አንችልም ነበር፦ የመጣነው ከየት ነው? ሰዎች የሚሞቱት ለምንድን ነው? (ዘፍጥረት 2:7, 17) በተጨማሪም በዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ላይ፣ ይሖዋ እንደ እኛ ዓይነት ስሜት ካላቸው ሰዎች ጋር የነበረውን ግንኙነት የሚያሳዩ ታሪኮችን ማግኘት እንችላለን።​—ያዕቆብ 5:17

  • ጠቃሚ የሆኑ ምክሮች። የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ክፍል የሆኑት የምሳሌና የመክብብ መጻሕፍት ጊዜ የማይሽራቸውና ጥበብ ያዘሉ ምክሮችን ይዘዋል። ለአብነት ያህል፣ አስደሳች የቤተሰብ ሕይወት መምራትና (ምሳሌ 15:17) ለሥራ ተገቢውን አመለካከት መያዝ ስለሚቻልበት መንገድ የሚገልጽ (ምሳሌ 10:4፤ መክብብ 4:6) እንዲሁም ወጣቶች ሕይወታቸውን ከሁሉ በተሻለ መንገድ እንዲጠቀሙበት የሚረዳ (መክብብ 11:9 እስከ 12:1) ምክር ይሰጣሉ።

በተጨማሪም በቶራ (የመጀመሪያዎቹ አምስት የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት) ውስጥ ተመዝግቦ የሚገኘውን የሙሴን ሕግ በማጥናት ጥቅም ማግኘት እንችላለን። ክርስቲያኖች ይህንን ሕግ እንዲጠብቁ ባይታዘዙም እንኳ በውስጡ ያሉት መመሪያዎች ደስተኛ ሕይወት ለመምራት እንድንችል ይረዱናል።​—ዘሌዋውያን 19:18፤ ዘዳግም 6:5-7

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ