የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 102
  • ቁማር ኃጢአት ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቁማር ኃጢአት ነው?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ አመለካከት
    ንቁ!—1995
  • ቁማር መጫወት ምን ስህተት አለው?
    ንቁ!—2002
  • በቁማር ወጥመድ ላለመያዝ መጠንቀቅ
    ንቁ!—2002
  • መጽሐፍ ቅዱስ ቁማርን ያወግዛል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 102
ቴሌቪዥን ላይ የሎተሪ ዕጣ ሲወጣ አንድ ቁማርተኛ ቲኬቱን እየተመለከተ

ቁማር ኃጢአት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ቁማር ዝርዝር ነገር ባይናገርም በውስጡ ከያዛቸው መመሪያዎች በመነሳት ቁማር ኃጢአት እንደሆነ መገንዘብ እንችላለን።—ኤፌሶን 5:17a

  • ቁማር የሚጫወቱ ሰዎች እንዲህ የሚያደርጉት በስግብግብነት መንፈስ ተገፋፍተው ነው፤ አምላክ ደግሞ ይህን ባሕርይ ይጠላል። (1 ቆሮንቶስ 6:9, 10፤ ኤፌሶን 5:3, 5) ቁማርተኞች ትርፍ ለማግኘት የሚመኙት በሌሎች ኪሳራ ነው፤ ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ የሌሎችን ንብረት መመኘትን ያወግዛል።—ዘፀአት 20:17፤ ሮም 7:7፤ 13:9, 10

  • በትንሽ ገንዘብም እንኳ ቁማር መጫወት በአንድ ሰው ልብ ውስጥ አደገኛ የሆነ የገንዘብ ፍቅር እንዲያቆጠቁጥ ሊያደርግ ይችላል።—1 ጢሞቴዎስ 6:9, 10

  • ቁማርተኞች አብዛኛውን ጊዜ የሚመኩት በአጉል እምነትና በዕድል ነው። ሆኖም አምላክ እንዲህ ያለውን እምነት እንደ ጣዖት አምልኮ ይመለከተዋል፤ ጣዖት አምልኮ ደግሞ ከእውነተኛው አምልኮ ጋር አብሮ ሊሄድ አይችልም።—ኢሳይያስ 65:11

  • መጽሐፍ ቅዱስ ያለምንም ልፋት የሆነ ነገር ለማግኘት ከመሞከር ይልቅ ጠንክሮ መሥራትን ያበረታታል። (መክብብ 2:24፤ ኤፌሶን 4:28) የመጽሐፍ ቅዱስን ምክር ተግባራዊ የሚያደርጉ ሰዎች ‘በድካማቸው ያገኙትን ይበላሉ።’—2 ተሰሎንቄ 3:10, 12

  • ቁማር ጤናማ ያልሆነ የፉክክር ስሜት ሊቀሰቅስ ይችላል፤ ይህ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተወግዟል።—ገላትያ 5:26

a በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቁማር በቀጥታ የተጠቀሰው የኢየሱስን ልብስ ለመከፋፈል ዕጣ ከተጣጣሉት በሌላ አባባል ቁማር ከተጫወቱት የሮም ወታደሮች ጋር በተያያዘ ብቻ ነው።—ማቴዎስ 27:35፤ ዮሐንስ 19:23, 24

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ